ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በኅልውና ዘመቻው ከፍተኛ ተጋድሎ ላደረጉ ሴት የሠራዊት አባላት እውቅና ሰጡ።

133

የካቲት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በኅልውና ዘመቻ ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ ላደረጉ ሴት የመከላከያ ሠራዊት አባላት እውቅናና የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሴቶች ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው።

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በዚህ ወቅት “ሴቶች በእናንተ ድርብ መስዋእትነት ሀገር ትቀጥላለችና፣ የሚገባችሁን ክብር መስጠት የኹላችንም ግዴታ ነው” ብለዋል።

በተለይም ሴቶች በጦርነት ወቅት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንደሚያጋጥማቸው የገለፁት ፕሬዚዳንቷ፤ በሰላም እጦት ትልቁን መከራ የሚያዩት ሴቶች እንደኾኑ ተናግረዋል።

የሀገራቸውን ዳር ድንበርና የሕዝባቸውን ደኅንነት ለማስጠበቅ ሲሉ ሕይወታቸውን መስዋእት ከማድረግ ባለፈ፤ በጦርነት ወቅት ልጆቻቸውን ለማዳን አካባቢያቸውን ጥለው እስከመሰደድ እና ለተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች እስከመጋለጥ ይደርሳሉ ብለዋል።

በኅልውና ዘመቻው ወቅት ሴት ጀግና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ያሳዩት ተጋድሎ እጅግ የሚደነቅ መኾኑንም አንስተዋል።

ሴቶች በሰላምና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቷ፤ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሴቶችን ወደ አመራርነት የማምጣት ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር መጋቢት 4 እንደሚፈጸም ቤተክርስቲያኗ አስታወቀች።
Next articleየቀድሞው የሰሜን ሸዋ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ሐሙስ እንደሚከናወን የሰሜን ሸዋ ሀገረስብከት አስታወቀ።