
የካቲት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን እሁድ መጋቢት 4/2014 ዓ.ም እንደሚፈጸም ቤተክርስቲያኗ አስታወቀች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ ሥርዓተ ቀብራቸውን ለማስፈፅም ቤተክርስቲያኗ የተለያዩ ኮሚቴዎችን አቋቁማለች።
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሥርዓተ ቀብር መርኃግብሩ ቅዳሜ ከጠዋቱ 3 ሰዓት በመስቀል አደባባይ ሽኝት በማድረግ ይጀመራል።
ከሰንብት በኋላ ወደ በመንበረ ፓትሪያሪክ የጸሎትና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።
መጋቢት አራት በሚካሄደው ሥርዓተ ቀብር ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሃይማኖቱ ተከታዮች እና ሌሎችም በተገኙበት በመንበረ ፓትሪያሪክ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የብፁዕነታቸው ሥርዓተ ቀብር በክብር ይፈጸማል ሲሉ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J