ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ ሻምበል መማር ጌትነት የክስ መዝገብ ጥፋተኛ በተባሉ ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

506

የካቲት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከሰኔ 15 ክስተት ጋር ተያይዞ ከሕዳር 23/2012 ዓ.ም ጀምሮ ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ሲታይ የቆዩ ተጠርጣሪዎች ጥፋተኛ በተባሉ 31 ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ጥፋተኛ በተባሉ 31 ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ችሎቱ በእያንዳንዳቸው ተከሳሾች ላይ ከእድሜ ልክ እስከ 15 ዓመት ጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ ነው ያስተላለፈው፡፡

ከቅጣት ውሳኔው በፊት በተከሳሾች የቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ተቀብሎ የመረመረው ችሎቱ ለአራት ተከሳሾች አምስት ማቅለያዎችን፣ ለ20 ተከሳሾች አራት ማቅለያዎችን፣ ለአራት ተከሳሾች ሦስት ማቅለያዎችን እና ጉዳያቸው በሌሉበት ሲታይ የቆዩ ሦስት ተከሳሾችን ደግሞ አንድ ማቅለያ ተቀብሏል፡፡

ማኅበራዊ አገልግሎት፣ የቤተሰብ ኀላፊነት፣ ሕመም፣ ወንጀሉን ከመፈጸማቸው በፊት የነበራቸው ለሀገር የተከፈለ ዋጋ እና ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መኾኑ በቅጣት ማቅለያነት ታይቷል፡፡

ችሎቱ ጉዳያቸው በሌሉበት ሲታይ የቆየውን የሻምበል መማር ጌትነት፣ በላይሰው ሰፊነው እና ልቅናው ይሁኔ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በሌሎች 28 ተከሳሾች ላይ ደግሞ ከ15 ዓመት እስከ 18 ዓመት ጽኑ እስራት አስተላልፏል፡፡

18 ተከሳሾች በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት፣ ሁለት ተከሳሾች በ15 ዓመት ጽኑ እስራት፣ ሁለት ተከሳሾች 16 ዓመት፣ አራት ተከሳሾች በ18 ዓመት እና ሁለት ተከሳሾች በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በፀጥታ እና ደኅንነት፣ በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በሰላም ማስከበር በትብብር ለመሥራት ተስማሙ።
Next articleየብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር መጋቢት 4 እንደሚፈጸም ቤተክርስቲያኗ አስታወቀች።