
የካቲት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ በ 5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ያስገነባውን የፕሮጀክቱ ማስፋፊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት አስመርቋል።
ፋብሪካው በ2003 ዓ.ም በ40 ሚሊዮን ብር ካፒታል፣ በ26 ሠራተኞች እና በ30 ሺህ ቶን የማምረት አቅም ነበር ሥራ የጀመረው። አዳማ ቆርቆሮ በ2006 ዓ.ም በ22 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ማስፋፊያ የማምረት አቅሙን ወደ 254 ሺህ ቶን አሳድጓል።
ከ2008 እስከ 2014 ዓ.ም ተጨማሪ የ5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ማስፋፊያ አድርጓል። በድምሩ በ7 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የግንባታ ወጭ የተገነባው ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ሳያመርት ለሦስት ሺህ ሠራተኞች የሥራ እድል የሚፈጥር ሲኾን፤ የማምረት አቅሙን ወደ 1 ሚሊየን 204 ሺህ ቶን ከፍ አድርጓል።
ፋብሪካው በኦሮሚያ ክልል በገላን ከተማ በ2013 ዓ.ም በ 11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ማስፋፊያ በማከናወን ላይ ይገኛል።
በአጠቃላይ በብረታ ብረት ዘርፉ የሚኖረው ኢንቨስትመንት 19 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር፣ የሠራተኞች ቁጥር 4 ሺህ 500፣ የማምረት አቅሙን ደግሞ 1 ሚሊየን 804 ሺህ ቶን ለማድረስ እየሠራ ይገኛል።
በብረታ ብረት ኢንዱስትሪው ውስጥ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣትና የግንባታ ቴክኖሎጂ እንዲሁም ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የኾነ አመራረት ሂደትን በመጠቀም ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብን ዓላማ ያደረገው ፋብሪካው በ2030 እኤአ ከውጭ ሀገር የሚገቡ የብረታ ብረት ምርቶችን በጥራት አምርቶ በመተካት በኢንዱስትሪው ዘርፍ በሀገር ውስጥና በምሥራቅ አፍሪካ ተመራጭ ፋብሪካ ለመኾንም እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ለአካባቢ ተስማሚ የኾነ የአመራረት ሂደትን በመጠቀም ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻልና በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ውስጥ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታጠቅ፣ በዘርፉ የኢንዱስትሪ ልህቀት ማእከል መኾን እና ኹሉን አቀፍ ማኅበራዊ ኀላፊነትን መወጣት የቀጣይ ዐብይ ተግባርም ነው ተብሏል።
ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ -ከአዳማ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/