አምባሳደሮች የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ስርዓትን እና መርህን በመከተል በተለያዩ መስኮች ለሀገራቸው ጥቅም እና ፍላጎት መሥራት እንዳለባቸው ም/ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

170

የካቲት 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት ሁለት የሳምንታት ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

በስልጠናዉ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የኢፊዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አምባሳደሮች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

አቶ ደመቀ በሰጡት የሥራ መመሪያ ኢ-ተገማች እና ተለዋዋጭ በሆነዉ የዓለም ፖለቲካ ኢኮኖሚ ስርዓት ዉስጥ በዚህ ደረጃ እራስን በማብቃት በየመድረኩ ሀገራዊ ጥቅምን ማስከበረን እና ግንኙነትን ማስፋት ይገባል ብለዋል።

የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ስርዓትን እና መርህን በመከተል በተለያዩ መስኮች አምባሳደሮች ለሀገራቸው ጥቅም እና ፍላጎት መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። ዓለማዊ ሁኔታዉን ቀድሞ የመረዳት እና ለዚህ ደግሞ ፈጣን ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አፍሪካዊ ወንድማማችነትን ማጠናከር እና በአፍሪካ አህጉር ያሉ አቅሞችን መጠቀም የሀገሪቱን ተሰሚነት እና ተደማጭነት እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪነት ለማሳደግ አምባሳደሮች በሚመደቡባቸው ሀገራት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።

አምባሳደሮቹ በሚመደቡባቸው ሀገራት ሁሉ የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ ወንድማማችነትን በመፍጠር ዓለም ኢትዮጵያን እንዲረዳ የማድረግ ትልቅ ሀገራዊ ኀላፊነት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

የዓለምን ነበራዊ ሁኔታን ያገናዘበና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሀገርን የሚያኮራ ሥራ እንዲያከናውኑ አቶ ደመቀ አስገንዝበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው ሥልጠናው ከሃያ በሚበልጡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰው በዋናነት ዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ የሁለትዮሽና ባለ ብዙ ወገን ዲፕሎማሲ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም፣ የሳይበር አጠቃቀም እንዲሁም ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ላይ ትኩረት በማድረግ ተሰጥቷል ብለዋል።

ስልጠናውን የተከታተሉ አምባሳደሮች በበኩላቸው ሥልጠናው የሀገሪቷንና የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ እንደተሰጣቸውና በዚህም የተጣለባቸውን ኀላፊነት በእውቀት ለመፈጸም እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ህዝባቸዉን ሀገሪቱ የሰጠቻቸዉን ተልዕኮ ለመፈፀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ:–አንዷለም መናን

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleትጋት፡ ከመርቆሪዎስ እስከ መርቆሪዎስ!
Next articleዜና ዕረፍት