“የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ተግባራት በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ኹሌም አሉ” የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

250

የካቲት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ላለፉት 40 ዓመታት ሰብዓዊ ሥራዎችን ሲሠራ የቆየው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት በጋራ በሚሠሩባቸው ክህሎት እና ሥራ ፈጠራን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የሰዎች ለሰዎች ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያከናወናቸው ሥራዎች ብዙ ችግሮችን የቀረፉ እና በኹላችንም ልብ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ድርጅቱ በትምህርት እና በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በተለይም በገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማቅለል ትልቅ ውጤት እንደማስመዝገቡ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር መሥራቱ ሀገራዊ ጥቅሙ ከፍተኛ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ይልማ ታዬ ድርጅቱ የተቀናጁ ሥራዎችን በመላው ኢትዮጵያ እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል። በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በሥራ ፈጠራ ዘርፍ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር ለመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በስፋት በሚሠራባቸው በሥራ ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም ብቁ ባለሙያዎችን በውጭ ሀገራት ሥራ ለማሰማራት ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት ጋር በጋራ ይሠራል ብለዋል፡፡

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት የቦርድ አባል እና ቃል ዐቀባይ ሰባስቲያን ብራንድስ (ዶ.ር) ድርጅቱ በግብርና የሐረር አማሮ ቴክኒካል ኮሌጅ ፣ በተፈጥሮ ሀብት አጠባበቅ የኖኖ ቤንጃ እና ወግዲ ወረዳዎች ፣ በሥራ ፈጠራ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተገኙ ውጤቶችን በአብነት ጠቅሰዋል።

ግብርናን በማዘመን ከግብርና ኮሌጆች ጋር በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ገበያው የሚፈልጋቸውን ሙያዎች በማሰልጠን በኩል ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ለመሥራት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡

እንደ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ባለፉት 40 ዓመታት በኢትዮጵያ 460 ትምህርት ቤቶችን የሠራ ሲሆን 8 የሞያ ማሰልጠኛ ኮሌጆችንም ገንብቷል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleከጥረት እስከ ንጋት
Next articleከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ