ኢየሩሳሌም የሕፃናትና ማኅበረሰብ ልማት ድርጅት በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ያሉ ሴቶችን ለማቋቋም እየሠራ መኾኑን ገለጸ፡፡

127

ባሕር ዳር፡ የካቲት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢየሩሳሌም የሕፃናትና ማኅበረሰብ ልማት ድርጅት በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ያሉ ሴቶችን በማቋቋም ራሳቸውን እና ወገናቸውን እንዲጠቅሙ እየሠራ መኾኑን ገልጿል፡፡

ድርጅቱ የሥራ ሥልጠና በመስጠት ሴቶች ከነበረባቸው ችግር ወጥተው ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግም ችሏል፡፡ የማቋቋም ሥራው የሚከናወነው በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በኩል ከስዊድን መንግሥት በተገኘ ድጋፍ እንደኾነም ተገልጿል።

አሚኮ ያነጋገራት ሰልጣኝ እንዳለችው ከድርጅቱ ስልጠና በመውሰድ ወደ ሥራ በመግባቷ ከነበረችበት ችግር መውጣት ችላለች፤ ከሥራዋ በተጓዳኝ ትምህርቷን እየተከታተለች ነው፤ እህቷንም በማስተማር ላይ ትገኛለች፡፡

በተለያዩ ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ውድድሮችም በመሳተፍ ሜዳሊያ ለማግኘት መብቃቷንም ነው የገለጸችው።

የኢየሩሳሌም የሕፃናትና ማኅበረሰብ ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ገብሩ ድርጅቱ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ የነበሩ 129 ሴቶችን ለማቋቋም በአምስት ዙር ሥልጠና መስጠቱን ተናግረዋል። ለሦስት ወራት በሥነ ልቦና፣ በሕይወት ክሕሎት እና በመሠረታዊ የንግድ ክሕሎት ሥልጠና የወሰዱት እነዚህ ሴቶች በድርጅቱ የመቋቋሚያ ገንዘብ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አመላክተዋል።

ወደ ሥራ ከገቡ በኋላ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ውጤታማነታቸው ይገመገማል ያሉት አቶ ሙሉጌታ በዚህ ዓመት 200 ሴቶችን ራስ ለማስቻል እንደሚሠራም ነው ያስረዱት። ከዚህ በፊት ሥልጠና ወስደው ወደ ሥራ የገቡ ሴቶች ከነበሩበት አስቸጋሪ ሕይወት ተላቀው የራሳቸውን ሥራ በመሥራት ውጤታማ እንደኾኑም ገልጸዋል።

ድርጅቱ ለአምስተኛ ዙር ያሠለጠናቸውን 53 ሴቶችም አስመርቋል፡፡

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሕገ ወጥ ግብይትንና ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር እየናረ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለመግታት የመንግሥት አስፈፃሚዎች ኀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል” የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር)
Next articleከጥረት እስከ ንጋት