
ጎንደር: የካቲት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከገቢዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ኮንትሮባንድን እና ሕገ ወጥ ንግድን ለመከላከልና የኑሮ ውድነትን ለማስተካከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጎንደር ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው።
መድረኩን የመሩት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) ሕገ ወጦች በተናጠልና በመደራጀት ምርት በመደበቅና በማከማቸት ሕዝብን እያማረሩ ይገኛሉ ብለዋል።
ምክትል ርእስ መሥተዳድሩ እንዳሉት ለኑሮ ውድነቱና ለዋጋ ንረት መባባስ ሕገ ወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ ትልቅ እንቅፋት ከመኾኑም በላይ ሕጋዊ ነጋዴዎችን እያዳከመ ነው። ለዚህም የመንግሥት የአስተዳደር ሥርዓትና አስፈፃሚዎች ሕገ ወጥነትን ሊቆጣጠሩ ባለመቻላቸው መኾኑን ዶክተር ጌታቸው ተናግረዋል።
“ሕገ ወጥ ግብይትንና ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር እየናረ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለመግታት የመንግሥት አስፈፃሚዎች ኀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል” ነው ያሉት፡፡
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ቀለመወርቅ ምህረቴ በስግብግብ ነጋዴዎች የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት እየተናጋ በመኾኑ ኹሉም መረባረብ ካልተቻለ ማስቆም አይቻልም ብለዋል።
የምክክሩ ተሳታፊዎች የኑሮ ውድነቱና የዋጋ ንረቱ መፍትሔ ካልተቀመጠለት ሕዝብን ከማማረር አልፎ ለሀገር ትልቅ ስጋት ይኾናል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡- አገኘሁ አበባው-ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/