
የካቲት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው በሳዑዲ እስር ቤቶች እና በዩክሬን ጦርነት ቀጣና ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለመታደግ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
በሳምንቱ አጋማሽ 139 ዜጎችን ከኬንያ መመለስ መቻሉንም አንስተዋል።
ከወቅቱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞም በግጭት አካባቢዎች ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለመታደግ በአውሮፓ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በቅርበት እየሠሩ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የህዳሴ ግድብ ኀይል ማመንጨት መጀመሩን ተከትሎ የግብጽ መንግሥት ለመንግሥታቱ ድርጅት የተቃውሞ ደብዳቤ መፃፉን በማስመልከት ለተጠየቁት ጥያቄ አምባሳደር ዲና በሰጡት ምላሽ የተለመዱ አፍራሸ አቋሞች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
እስካሁንም የግድቡ ግንባታ የ2015 የመርሆዎች ስምምነትን ተከትሎ እየተከናወነ መኾኑን አስታውሰው
“ስምምነቱ ኃይል ከማመንጨት ከማከናወን አይገድበውም” ብለዋል።
ተቋርጦ የቆየው የሦስትዮሽ ድርድር በቅርብ ጊዜ ሊጀመር እንደሚችልም ጠቁመዋል።
ውጫዊ ጫና ለመመከት ውስጣዊ የፐብሊክ ዲኘሎማሲ አቅምን ለማሳደግ እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል። መደበኛውን ዲፕሎማሲ በፐብሊክ ዲኘሎማሲ የመደገፍ ሥራ እየተከናወነ መኾኑን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በዩኒቨርሲቲዎች እየተቋቋሙ ያሉ የፐብሊክ ዲኘሎማሲ ማዕከላት የዚሁ አካል ናቸው ብለዋል።
በመግለጫቸው ላይ ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪና ሴሬኒ የተመራ የልዑካን ቡድንን ጋር መወያየታቸውን አስታውሰዋል።
የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የጣሊያን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ላለው የልማት ትብብር ቀጣይነት ያመላከተ ነው ብለዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሶማሊያ ልዩ ልዑክ ጀምስ ስዋን ጋር መወያየታቸውንም አስታውሰዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/