ከ100 ሺህ በላይ በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየተሠራ ነው።

209

የካቲት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ አረቢያ በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ ከ102 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በቀጣይ ሦስት ሣምንታት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ እየተሠራ መኾኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

በሳዑዲ አረቢያ ከ750 ሺህ በላይ የሚኾኑ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩ ሲኾን ከ450 ሺህ በላይ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ እንደሚኖሩ መገለጹን ፋብኮ ዘግቧል።

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ለማስመለስ አስፈጻሚ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ ይገኛልም ነው የተባለው።

የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን፣ ጤና ሚኒስቴር ፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በአጠቃላይ ከ16 በላይ የሚኾኑ ተቋማት የኮሚቴ አባል ናቸው፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
Next articleበክልሉ በመስኖ ልማት ተስፋ ሰጪ የበጋ ምርት መመልከታቸውን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ተናገሩ።