የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

672

ባሕር ዳር: የካቲት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

ቅዱስነታቸው ሰሞኑን ባደረባቸው ህመም የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው መቆየቱ ይታወሳል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በ1980 ዓ.ም ነሐሴ 29 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ተብለው የተሾሙ ሲሆን ላለፉት 34 ዓመታት በፓትርያርክነት አገልግለዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአድዋ ድል በመላው ጥቁር ሕዝቦች ዘንድ ዘመን ተሸጋሪ የአሸናፊነት መንፈስን ያላበሰ ታላቅ ገድል ነው ሲሉ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ፡፡
Next articleፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።