የአድዋ ድል በመላው ጥቁር ሕዝቦች ዘንድ ዘመን ተሸጋሪ የአሸናፊነት መንፈስን ያላበሰ ታላቅ ገድል ነው ሲሉ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ፡፡

131

እንጅባራ: የካቲት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 126ኛው የአድዋ ድል በዓል በዩኒቨርሲቲው ’’የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ኅብረት ለአፍሪካውያን የነፃነት ጮራ’’ በሚል መሪ ሃሳብ በፓናል ውይይትና በልዩልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል፡፡

የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ብሔራዊ ክብርና ኩራትን ያጎናፀፈ፣ ለመላው አፍሪካውያን ደግሞ ለነፃነታቸው ትግል መነሻና ብርታት የሆነ ታላቅ ድል ነው ተብሏል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ክንዴ ብርሃን የአድዋ ድል በመላው ጥቁር ሕዝቦች ዘንድ ዘመን ተሸጋሪ የአሸናፊነት መንፈስን ያላበሰ፤ ነጮች በጥቁሮች ላይ የነበራቸውን የተዛባ አስተሳሰብ የቀየረ ታላቅ ድል ነው ብለዋል፡፡

አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ለ40 ዓመታት ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር ዝግጅት ያደረገበትን ጦርነት በአጭር ጊዜ ለመቋጨትም ሚስጥሩ የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ያወረሰው የአሸናፊነት መንፈስ ነውም ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንቱ፡፡
በዩኒቨርሲቲው የታሪክ መምሕር ዶክተር አየነው ፈንታ ወጣቱ ከአድዋ በመማርና ስኬቶችን በማጎልበት የታሪክ ቅብብሎሹን ሊያስቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ሳሙኤል አማረ- ከእንጅባራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ በተካሔደው ትግል የአማራ ሕዝብ ስንቅ እና ትጥቅ ለጸጥታ ኀይሉ በማቅረብ እና በቀጥታ በመፋለም የማይተካ ሚና አበርክቷል”
Next articleየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።