“አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ በተካሔደው ትግል የአማራ ሕዝብ ስንቅ እና ትጥቅ ለጸጥታ ኀይሉ በማቅረብ እና በቀጥታ በመፋለም የማይተካ ሚና አበርክቷል”

118

ባሕር ዳር: የካቲት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮና ተጠሪ ተቋማትን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ላይ ወይይት አካሂዷል።

በውይይቱም የአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮንና ተጠሪ ተቋማት ኀላፊዎች፣ የኹሉም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና የምክር ቤቱ ልዩ ልዩ አማካሪዎች ተሳትፈዋል።

የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ኮማንደር መንገሻ አውራሪስ እንዳሉት አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ በተካሔደው ትግል የክልሉ ሕዝብ ስንቅ እና ትጥቅ ለጸጥታ ኀይሉ በማቅረብ እና በቀጥታ በመታገል ከፍተኛ ተሳትፎ አድርጓል።

ወጣቶች በአማራ ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመመከት በሀገር መከላከያ፣ በልዩ ኀይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ በመቀላቀል ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸው ተነስቷል።

ከዚህም በተጨማሪ አጠቃላይ በፍትሕ ተቋማት የተሠሩ ሥራዎች እና የታዩ ችግሮች በሪፖርቱ ተነስቷል።

በዚህ ወቅትም የጸጥታ መዋቅሩ የማኅበረሰቡን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ በተሳታፊዎች ተነስቷል።

በተለይም ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና የሰዎች ዝውውር መንግሥት ትኩረት እንዲሰጠው ተጠይቋል።

ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎችን ተከታትሎ ለሕግ የማቅረብ ሥራ በተደራጀ መንገድ ሊሠራ እንደሚገባ ተመላክቷል።

ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ አማራዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ከሌሎች ክልሎች የጸጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት ሊሠራ እንደሚገባም አባላቱ አስገንዝበዋል።

በክልሉ የተጠናከረ ፍተሻ እና የቁጥጥር ሥራ ሊከናወን ይገባልም ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleብሔራዊ ምክክር ለብሔራዊ መግባባት
Next articleየአድዋ ድል በመላው ጥቁር ሕዝቦች ዘንድ ዘመን ተሸጋሪ የአሸናፊነት መንፈስን ያላበሰ ታላቅ ገድል ነው ሲሉ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ፡፡