ምህረት የሕክምና መሳሪያዎች አቅራቢ ድርጅት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

148

ደሴ: የካቲት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ የሚገኘው ምህረት የሕክምና መሳሪያዎች አቅራቢ ድርጅት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሚውል ነው ተብሏል፡፡
ምህረት የሕክምና መሳሪያዎች አቅራቢ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ጺዮን ዓላዛር ድጋፉን ለወሎ ዩኒቨርሲቲ አስረከበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ኃላፊነቱን ወስዶ የተቀበላቸውን ድጋፎች ለጤና ተቋማት ያደርሳል ነው ያሉት፡፡
በጦርነቱ ምክንያት የደረሰውን ውድመት ጥናት ማድረጋቸውን ጠቁመው ማኅበረሰቡ የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ እንደኾነ እንገነዘባለን ብለዋል፡፡
ከ1 ሚሊዮን 500 ሽህ ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የጠቆሙት፡፡ ሌሎች አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየን (ዶ.ር) በአካባቢው ከደረሰው ጉዳት አንጻር ድጋፎች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡
ምህረት የሕክምና መሳሪያዎች አቅራቢ ድርጅት ዩኒቨርሲቲውን መርጦ ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲያደርስ የተሰጠውን ኀላፊነት እንደሚወጣም አረጋግጠዋል፡፡
ለተሰጣቸው ኀላፊነትና ለድጋፉ ምሥጋና ያቀረቡት ዶክተር መንገሻ በቀጣይነትም በዘላቂነት አብሮ ለመሥራት ዝግጁ እንደኾኑ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ:- ደጀን አምባቸው -ከደሴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleኅብረተሰቡ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት አሸባሪው ኦነግ ሸኔን በቁርጠኝነት እየታገለ እንደኾነ የደዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
Next article“እርር ቅጥል ቢሉም የእርሱ ጠላቶቹ፣ ምኒልክ ጀግና ነው እስከ ዘመዶቹ”