ኅብረተሰቡ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት አሸባሪው ኦነግ ሸኔን በቁርጠኝነት እየታገለ እንደኾነ የደዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

130

የካቲት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የደዋጨፋ ወረዳን በወረረበት ወቅት ተላላኪው ኦነግ ሸኔ አቀባበል በማድረግ በወረዳው ላይ ከፍተኛ ጥፋት አድርሷል፡፡
የደዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳዳሪ አብዱ መሐመድ ለአሚኮ እንደገለጹት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በወረዳው እና በአካባቢው በቆየባቸው ጊዜያት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰውን ተላላኪውን ኦነግ ሸኔን የወረዳው ሕዝብ ከውስጡ በመነጠል ለሕግ አሳልፎ እየሰጠ ይገኛል።
አቶ አብዱ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጋር በመቀናጀት በወረዳው 200 ሚሊዮን ብር የሚገመት የመንግሥት ተቋማትን ሃብት እና ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኢንቨስትመንት ሃብት መዝብሯል ብለዋል።
በወረዳው በሽብር ቡድኖቹ 106 ንጹሃን ወገኖች ሲሞቱ 140 መቁሰላቸውንም አስተዳዳሪው አስረድተዋል።
አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በሕዝብ ውስጥ በመደበቅ በሕዝብ ስም እያጭበረበረ ነው፤ ቡድኑ ሕዝብን በብሔር እና በእምነት በመነጣጠል ሃብት የሚያካብቱ የመሳሪያ ነጋዴና ዘራፊዎች ስብስብ ነው ያሉት አቶ አብዱ የሕዝብ ጠላት መሆኑን የራሱን ወገን በመድፈር፣ በመግደልና በመዝረፍ በተግባር እንዳሳየ አስረድተዋል።
ኅብረተሰቡ የአሸባሪ ቡድኑን ዓላማ በመገንዘብ እስከግብዓተ መሬቱ ለመታገል ቆርጦ ተንስቷል፤ እየታገለውም ይገኛል ነው ያሉት።
በኅብረተሰቡ ጥቆማ እና በጸጥታ መዋቅሩ ቅንጅታዊ ሥራ በወረዳው ከ300 በላይ ተጠርጣሪ የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዘጋቢ፡-ሥነ-ጊዮርጊስ ከበደ-ከደዋ ጨፋ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበዩክሬን ቀውስ ሁሉም ወገኖች ከግጭት አባባሽ ድርጊቶች እንዲታቀቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጥሪ አቀረቡ።
Next articleምህረት የሕክምና መሳሪያዎች አቅራቢ ድርጅት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡