“የዓድዋ ድል የተገኘው በእምዬ ምኒልክ ብልሀትና ጥበብ፣ በእቴጌ ጣይቱ ድፍረትና በሁሉም ኢትዮጵያውያን አርበኞች ተጋድሎ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር)

163

ባሕር ዳር: የካቲት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 126ኛው የዓድዋ የድል በዓል በደማቅ ሁኔታ በባሕር ዳር እየተከበረ ይገኛል፡፡ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) ዓድዋ ታሪክ ነው፣ ዓድዋ ነፃነት ነው፣ ዓድዋ ድል ነው፣ ዓድዋ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን የአፍሪካን ነፃነት ችቦ የለኮሰ ድል ነው ብለዋል፡፡
ድሉ የተገኘው በእምዬ ምኒልክ ብልሀት፣ ጥበብ፣ በእቴጌ ጣይቱ ድፍረትና በመላ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ተጋድሎ መኾኑን አንስተዋል፡፡
ዓድዋ ሌሎች ጥቁር ሕዝቦች ለነፃነታቸው እንዲነሳሱ በር መክፈቱን ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል፡፡


ዓድዋ የኢትዮጵያን አንድነት አጽንቶ በዓለም ሉዓላዊነቷ እንዲታወቅና እንዲረጋገጥ ያደረገ በመኾኑ ሁልጊዜ መዘከር ይገባናል ነው ያሉት፡፡
የዓድዋ የድል በዓል የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክሮ ዘላቂ ማድረግ የሚቻለው በመስዋእትነት መሆኑ ሁላችንም እንድንረዳ ትውልዱም እንዲያውቅ የሚያስተምር በመኾኑ መዘከር ይገባናል ብለዋል፡፡
የዓድዋ በዓል የእምዬ ምኒልክና የእቴጌ ጣይቱ ስም ሳይነሳ በፍጹም ሊከበር አይታሰብም ያሉት ዶክተር ይልቃል ዓድዋና አፄ ምኒልክ እንዲሁም እቴጌ ጣየቱ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ብለዋል፡፡
መሪዎቻችንን ስናከብር የሀገራችንን አንድነት መጠበቅ እንችላለን ነው ያሉት፡፡ ዓድዋን በድል እንድንወጣው ያደረጉን መሪዎቻችን ታሪክ የመላ ኢትዮጵያውያን ታሪክ መኾኑንም ርእሰ መሠተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡ ዓድዋን በየዓመቱ ለማክበር በቂ ምክንያት እንዳለውም ነው የጠቆሙት።
የተያዘው ዓመት ለቀጣዩ ትውልድ እሴት ሆኖ የሚያገለግለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በመጀመሪያ ደረጃ የኀይል ማመንጨት የተቻለበት በመኾኑ ይህ ትውልድም እንደ ዓድዋ ታሪክ እየሠራ በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ዶክተር ይልቃል ገልጸዋል፡፡ የዓድዋ በዓል ሲከበር የመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል አስፈላጊ እንደኾነም አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የዓድዋ ድል በነፃዋ ሀገር የምናከብረው የነጻነት በዓል ነው” ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
Next articleሀገረ ምኒልክ የአፍሪካዋ ጃፓን ወይስ አፍሪካዊቷ ኤልዶራዶ?