“የዓድዋ ድል በነፃዋ ሀገር የምናከብረው የነጻነት በዓል ነው” ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

135

የካቲት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው፡፡ በፌዴራል ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው 126ኛው የዓድዋ ድል በዓል ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፉት መልእክት “የዓድዋ ድል በዓል በኢትዮጵያዊያን አባቶቻችን የተፈጸመ እና ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የተበረከተ የነፃነት ገጸ በረከት ነው” ብለውታል፡፡
ድሉ ከቅኝ ግዛት ይልቅ ሞት ይሻለናል ባሉ ቀደምት አባቶች የተፈጸመ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቷ ዛሬም የዓድዋን መንፈስ እና ቅርስ መውረስ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
የዚያ ትውልድ የጀግንነት አበርክቶ ከሀገር ውስጥ ችግሮቻችን አልፎ ለአፍሪካዊያን እና ለመላው ጥቁር ሕዝብ አንድነት እርሾ ሆኗል ያሉት ፕሬዝዳንቷ የአሁኑ ትውልድ የዓድዋን ድል ከማክበር በተጨማሪ በእለት ከእለት ሕይዎቱም ሊኖርበት ይገባል ነው ያሉት፡፡
ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ በመልእክታቸው የነጻነት ትርጉሙ የሚገባን በባርነት እና በቅኝ ግዛት ቀንበር ውስጥ ያለፉ ሀገራትን ስንመረምር ነውም ብለዋል፡፡ በዓሉ በብሔራዊ ደረጃ ሲከበር ለትውልዱ የሚያሻግረው ትውፊት ስላለው ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ ታሪክን ለጊዜያዊ ፍላጎታችን ብቻ ከመጠቀም መቆጠብ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
“የዓድዋ ድል በነፃዋ ሀገር የምናከብረው የነፃነት በዓል ነው” ያሉት ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ድሉ በአጤ ምኒልክ በሳል አመራር እና በሚመሩት ሕዝብ ቀናዒነት እና እስከ ሞት በደረሰ መስዋእትነት የተገኘ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም ልዩነቶቻችንን አክመን፣ ጉዳቶቻችንን ጠግነን እና ክፍቶቻችንን ሞልተን በዓሉን ለማክበር በአንድነት ልንቆም ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የዓድዋ የድል በዓል ከሀገር ውጭም በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ እየተከበረ ነው” ባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር
Next article“የዓድዋ ድል የተገኘው በእምዬ ምኒልክ ብልሀትና ጥበብ፣ በእቴጌ ጣይቱ ድፍረትና በሁሉም ኢትዮጵያውያን አርበኞች ተጋድሎ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር)