
የካቲት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 126ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነው የሚገኘው፡፡ በመርኃግብሩ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ባስተላለፉት መልዕክት “በአያቶቻችን ተጋድሎና በከፈሉልን መስዋእትነት ኢትዮጵያውያን ለዚህ ደርሰናል” ብለዋል፡፡ አጤ ምኒልክ የዛሬ 126 ዓመት የሀገሬው ሕዝብ ከመላው ኢትዮጵያ ተነስቶ ወረኢሉ ላይ እንዲገኝ መልዕክት ሲያስተላልፉ በመጀመሪያ አመላችሁን በጉያችሁ አድርጉ ማለታቸውን አስታውሰዋል፡፡
ይህም በሀሳብ የማይግባቡ ነገር ግን በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ በአንድነት እየተሳሳቁ፣ እየተዛዘኑ እና እየተደጋገፉ እንዲሄዱ አድርጓቸዋል ነው ያሉት፡፡
በዓድዋው ጦርነት ከኢትዮጵያ አንድም ተዋጊ አልተማረከም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ኢትዮያውያን ይህንን ታሪክ ይዘው በልዩ ልዩ አውደ ውጊያዎች ትልቅ ገድል መፈጸማቸውን አብራርተዋል፡፡ ፋሽስት ጣልያን ዳግም ኢትዮጵያን በደፈረ ጊዜም አያቶቻችን አምስት ዓመት ሙሉ በየተራራው፣ በየሸንተረሩ ተጋድሎ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡ ጣልያናውያን የዓድዋን ጦርነት ኢትዮጵያ እንዳሸነፈች በሰሙ ጊዜ በአንድ በኩል የእምዬ ምኒልክን ምስል በአንድ በኩል የእቴጌ ጣይቱን ምስል አድርገው ቪቫ ምኒልክ ቪቫ ጣይቱ በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል፤ ወራሪዎች ከአፍሪካ እንዲወጡም የተናገሩበት ቀን ነው፡፡
ይህ ትልቅ ድል መኾኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሕንን ድል በትንሹ እና በቀላሉ ማየት እንደማይገባው አሳስበዋል፡፡
ከመላው ጥቁር ሕዝብ መካከል ለዓለም ሕዝብ የአፍሪካን ታሪክ በወርቅ ብዕራቸው የጻፉ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ የዓድዋን ጦርነት የማሸነፍ ምልክቱም አንድ መሆን ነው ብለዋል ልጅ ዳንኤል፡፡ እኛ ደጋግመን እንደምንናገረው አንድነት በጦርና በጠብ መንጃ፣ በመድፍና በመትረየስ ብቻ መሆን የለበትም ብለዋል፡፡ ልጅ ዳንኤል ጆቴ እንዳሉት አሁንም ኢትዮጵያ እድትፈርስ፣ እንድትወድቅ እና እንድንበረከክ የሚፈልጉ ኀይሎች አሉ ብለዋል፡፡ አንድነታችንን አጠናክረን ካልጠበቅን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተደረገው ሙከራ ሊደገም እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም ሀገራዊ ሰላምና እና አንድነትን ማስከበር ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ልጅ ዳንኤል እኛ ዛሬ ልጆቻችንን በሚገባ ካላስተማርን፣ ታሪካቸውን አውቀው እንዲያድጉ ካልተደረገ በስተቀር የጠላቶቻችን መሳለቂያ እንሆናለን፤ ሀገራችንንም ወደ ኋላ እናስቀራታለን ብለዋል፡፡ “ሥነ-ምግባርን እና ግብረ-ገብነትን ያልተማረ ማንኛውም ወጣት የወደፊቷ ኢትዮጵያ መከራ ነው ሚሆነው” በማለትም ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸውን ታሪክ እንዲያስተምሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/