የሩሲያና አሜሪካ ኤምባሲዎች ለ126ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

149

የካቲት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገሩን ከአውሮፓውያን ቅኝ ገዢዎች በመታደግ ነጻነቱን ያስከበረበት መኾኑን በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተርክሂን ገለጹ።
የዓድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያ የነጻነት ምልክት ነው ብለዋል።
አምባሳደር ኤቭጌኒ ተርክሂን 126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የዓድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያ የነጻነት ምልክት ነው፤ ድሉ የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት በማጠናከር ኢትዮጵያ የራሷ የሀገር ውስጥና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲኖራት ያደረገ ጠንካራ ኀይል እንደኾነም ገልጸዋል።
“የዓድዋ ጦርነት ያለ ምንም ማጋነን በባርነት ይኖሩ ለነበሩ የአፍሪካ ሕዝቦች ከቅኝ ግዛት ቀንበር ለመላቀቅ ላደረጉት ትግል መሪ ኮከብ ነበር” ብለዋል።
የዓድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያና የሩሲያ ግንኙነት የመጀመር ሂደት ውስጥ ታሪካዊ ስፍራ እንዳለው አመልክተዋል።
“የሩሲያ ተወካዮች በጦር ሜዳ ለተገኘው ድል በግላቸው አስተዋጽኦ አድርገዋል” ያሉት አምባሳደሩ፤ የሩሲያ ሕክምና ባለሙያዎች በጦርነቱ የቆሰሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሕይወት በማዳን እርዳታ እንዳደረጉ ተናግረዋል።
የዓድዋ ጦርነት መጠናቀቁን ተከትሎ ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመራቸውንና የዓድዋ ድል በኹለቱ ሀገራት የግንኙነት ታሪክ ጠንካራ መሰረት መኾኑን ገልጸዋል።
አምባሳደር ሰርጌይ ተርክሂን በዚህ ታሪካዊ ቀን ለኢትዮጵያ ወንድም ሕዝብ ሰላም፣ ብልጽግናና ስኬትን እንደሚመኙ መግለጻቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲም በዓሉን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያዊያን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የዓድዋ አርበኞች የነፃነት ጀምበር እንድትወጣ በከፈሉት መሰዋእትነት ዛሬም እንዘክራቸዋለን” ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ
Next article“ሥነ-ምግባርን እና ግብረ-ገብነትን ያልተማረ ማንኛውም ወጣት የወደፊቷ ኢትዮጵያ መከራ ነው የሚሆነው” ልጅ ዳንኤል ጆቴ