“የዓድዋ አርበኞች የነፃነት ጀምበር እንድትወጣ በከፈሉት መሰዋእትነት ዛሬም እንዘክራቸዋለን” ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ

131

ባሕር ዳር: የካቲት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ በምኒልክ አደደባባይና በዓድዋ ድልድይ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ “የእኛ አያቶችና ቅድመ አያቶች በዓድዋ በፈጸሙት ገድል ለዛሬ ማንነታችን፤ ላልተበረዘ ባሕልና እሴቶቻችን፤ የሉዓላዊት ሀገር ኢትዮጵያ ባለቤት እንድንኾን አስችሎናል” ብለዋል፡፡
ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ሀገራቸው በልባቸው ስለታተመች ሁለመናቸውን ለመስጠት ቆርጠው በመነሳት ጠላትን ድል ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ አርበኞቹ የኢትዮጵያ ፍቅር በደማቸው የተዋሀደ፣ ሀሳባቸው የተዛመደ፣ አጥንታቸው የተሳሰረ ገድላቸው በትውልድ ልብ ውስጥ የተከበረ፣ የነፃነት ጀምበር እንድትወጣ በከፈሉት መሰዋእትነት ዛሬም እንዘክራቸዋለን ብለዋል፡፡
“የሁላችንም ቤት የኾነችው የሀገሪቱ ርእሰ መዲና አዲስ አበባ ዓድዋን ለዘላለም የምትዘክርበት ሀውልት፣ ድልድይ እና አደባባይ አላት” ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር፡፡
የአሁኑ ትውልድ ዓድዋን ለመዘከር የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጫፎች የርቀት ልኬታ መነሻ፤ ግዙፉን የአድዋ የድል ታሪክ የሚዘክር ሁሉን አቀፍ ሕንፃ ዓድዋ ዜሮ ዜሮ በመገንባት ላይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ዓድዋ ፍትሕን በአደባባይ ያስገኘ የእውነት የፍትሕ ችሎት መኾኑን ምክትል ከንቲባው ጠቁመዋል፡፡ ዓለም ፍትሕ እውነት ሳይኾን ጉልበት፣ ሀቅ ሳይኾን ኢኮኖሚ መኾኑን በግልጽ አሳይቶናልም ብለዋል፡፡ ለዚህም ጠንክሮ መሥራት እና ድህነትን ማሸነፍ አስፈላጊ እንደሆነ በአጽኖት ተናግወረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ብሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን በሑመራ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
Next articleየሩሲያና አሜሪካ ኤምባሲዎች ለ126ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።