
የካቲት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የካቲት 16/1885 ለሦስት ወር ያህል ውይይት በማድረግ ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ተሰብስበው ከ80 በመቶ በላይ የሚኾነውን የአፍሪካ መሬት የሐሳብ መስመር እያሠመሩ ያለ ከልካይ ተከፋፈሉ።
የበርሊን ጉባዔ በታሪክ አጥኚዎችና ፖለቲካ ተመራማሪዎች ዘንድ በአብዛኛው “አፍሪካን የመቀራመት ጉባዔ” ተብሎ ይታወቃል።
በጉባዔው ላይ የጀርመን፣ ኦስትሮ-ሀንጋሪ፣ ቤልጅየም፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖርቹጋል እና የጣልያን ተወካዮችም ተገኝተዋል። ይህን ተከትሎ ጣልያንም ኢትዮጵያን በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ ብትነሳም እምቢተኛው ጥቁር ሕዝብ ማንነቱንና ክብሩን አሳልፎ ላለመስጠት በመወሰኑ ያልተመጣጠነ ውጊያ ቢገጥመሙም አሳፍሮ መልሷታል።
ታሪክም ይህን ጦርነት “የዓድዋ ጦርነት” በማለት ለጥቁር ሕዝቦች ታላቅ መነቃቃትና ተስፋ የሰጠውን የጦርነቱን ድል ደግሞ “የዓድዋ ድል” ብሎ ሲዘክረው ይኖራል።
የታሪክ ምሁራን እንደሚያስቀምጡት የዓድዋ ጦርነት በአፍሪካ ምድር ከተከናወኑት ጦርነቶች ከፍተኛውን የዋጋና የክብር ሥፍራ ይዟል። አንድ አውሮፓዊ ጦር በአፍሪካውያን ጦር ሲሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ጦርነቱ ብዙ መልክና ብዙ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡
ዓድዋ ለአፍሪካ ምን ማለት ነው? ስንል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ የኾኑትን አዳነ ካሴ (ዶ.ር) ጠይቀናቸዋል። እንደ ተመራማሪው ማብራሪያ የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያ ነጻነትና ኩራት፣ በዓለም ዙሪያ በተለይ በአሜሪካዎቹ ሰፋፊ እርሻዎች ለ500 ዓመታት በባርነት ለተጋዙ ጥቁር ሕዝቦች ደግሞ የማንነት ማረጋገጫ፣ የዘመናት ጭቆናና የሥነ-ልቦና ቁስልን የሻረ የተስፋ ትንሣኤ ኾኖም ነበር። በአርነት ትግሉ መስክ በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩት እህት የአፍሪካ ሀገሮችም ኢትዮጵያ ፋና ወጊ ፍኖታቸውና የራዕይ ምንጫቸው ነበረች።
የዓድዋ ድል የፓን አፍሪካን ንቅናቄ መሠረት ነው ያሉት ዶክተር አዳነ በዓሉ የአፍሪካዊያን እንዲኾን መጀመሪያ እኛ በዓሉን የራሳችን እናድርገው ይላሉ።
ዓድዋ ላይ የተለኮሰው የድል ችቦ በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩት የአፍሪካ ሀገሮች ቀንዲል ኾኗል። ለዚህም ክብር ለመስጠት 17 የአፍሪካ ሀገሮች የሰንደቅ ዓላማ ቀለማቸውን ከኢትዮጵያ ወርሰዋል።
ዶክተር አዳነ “የዓድዋ ድል እኛ ስላቀለልነው አፍሪካውያን የእነሱ ሊያደርጉት አልቻሉም እንጂ ይህ ድል ከአፍሪካም አልፎ የዓለም ጭቁኖች ኹሉ የድል በዓል ኾኖ መከበር ይችል ነበር” ብለዋል፡፡ እናም ኹሉም የድርሻውን በመወጣት ታሪካችንን እና ታሪክ ሠሪዎቻችንን በማክበር ለዓለም ሕዝብ የድል ኩራታችንን ልናሳውቅ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አብነት እስከዚያ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/