
አዲስ አበባ: የካቲት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጀግኖቻችን እብሪተኛውን የጣልያን ጦር ድባቅ በመምታት ኢትዮጵያን እንዳይፈነጭባት ለማድረግ በደማቸዉ ታሪክን ጽሕፈዉ እንዳስቀመጡ ገልጸዋል፡፡ ዓድዋ የኢትዮጵያዉያን እና የአፍሪካዉያን የነጻነት ገድል የተፈጸመበት የድል ቀንም ነው ብለዋል፡፡
ጀግኖች አባቶቻችን በደማቸዉ የድል ዜና አሰምተዉናል፤ ጀግኖቹ በታሪካችን ላይ ዘውድ የደፉት ከጠላት ጋር ተናንቀው ህይወት ከፍለው ነው።
የዓድዋን ድል ያህል ግዙፍና የጥቁሮችን የባርነት ቀንበር ያወለቀ ገድልም በዓለማችን አልታየም ብለዋል፡፡ ዓድዋ ዓለም አቀፍ ግርማን ያገኘ፣ ታሪክን የቀየረ የዓለማችን ታላቅ ገድል ነው፤ ይህንን ግዙፍ ታሪክ የጋራ ማድረግ አቅቶናል ይላሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ እና ጥናት ምርምር መምህሩ ዶክተር አዳነ ካሴ፡፡
አድዋን ነግረው አይጨርሱትም፤ የጀግኖቻችን አልደፈር ባይነት እና የሥነልቦና ጥንካሬ የሚያሳይ ነዉ፤ ዘመናዊ ጦር ያልታጠቀች አንዲት ሀገር ዘመናዊ ጦር የታጠቀች አውሮፓዊት ሀገርን ጦር አሸነፈች? ቢያስብልም አባቶቻችን ግን ይህንን ገድል ፈጽመዋል ብለዋል፡፡
የሉዓላዊነት መገለጫ የሆነዉን አድዋን ከታሪክ ሽሚያ እና ከብሔር መነጸር አውጥቶ ማክበር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ የዓድዋ ድል ጥቁር ሕዝቦች ለአምባገነን ነጮች “አንገዛም!” በሚል ቁጣ ስለ ማንነታቸዉና ስለ ክብራቸዉ በጦር ፍልሚያ የታደጉበትና ክብራቸውን ያስጠበቁበት ጦርነት የወለደው ተዓምራዊ ገድል ነው ብለዋል።
ዓድዋ እምነት ሳይለይ፣ ወጣት፣ ጎልማሳ፣ አዛውንት፣ ሴት፣ ወንድ ሳይለይ ነጻነትን ከሕይወት በላይ የተተረጎመበት ዓለም አቀፍ ሰነድ መሆኑን አስግንዝበዋል፡፡
አርበኞች በዱር በገደል ተዋግተዉ በከፈሉት መስዋእትነት ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆኑ አፍሪካዉያንም ሉዓላዊነታቸዉን አስከብረዉበታል፡፡
ከታሪክ ሽሚያ ወጥቶ አድዋን አድዋ ያደረጉ ጀግኖችን ታሪክ ሰንዶ ማስቀመጥ እና በስማቸዉ የተሠሩ ማስታዎሻዎችን መጠበቅም ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን ዶክተር አዳነ ጠቅሰዋል፡፡
ዛሬ ላይ በነጻነት ሰንደቅ ስር ለመቆም ትናንት የተከፈለ ውድ ዋጋ አለ፤ በአድዋ ጦርነት ጀግኖች አጥንታቸዉን ከስክሰዉ ኢትዮጵያን እንዳቆዩ ሁሉ የጋራ ታሪካችንን አጽንተን ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ጠብቀን የጋራ ታሪክን መጻፍ እንደሚገባ ዶክተር አዳነ አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/