“የዓድዋ ድል በዓል ምኒልክ አደባባይ ይከበራል” የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር

370

አዲስ አበባ: የካቲት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በምኒልክ አደባባይ እንደሚያከብር እና ሕዝቡም በተለመደዉ መንገድ በዓሉን በአደባበዩ ለመታደም እንዲገኝ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ገለጸ፡፡

በዓሉ በምኒልክ አደባባይ እንደማይከበር የሚወራዉ ወሬም ከመረጃ ክፍተት እና አለመናበብ የመጣ ነዉ ብሏል ማኅበሩ፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ለአሚኮ እንደተናገሩት የዓድዋ ድልን እና ምኒልክን መለየት አይቻልም፡፡ አጤ ምኒልክ መላ ኢትዮጵያን አስተባብረዉ የበሰለ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራር ባይሰጡ ኖሮ የዓድዋ ድል አይኖርም ነበር፤ አጤ ምኒልክ በዓድዋ ድል መሪ ተዋናይ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ለኢትዮጵያ ብቻም ሳይኾን ለጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና የነጻነት ብስራት ስለኾኑ በዓሉ በእሳቸዉ አደባበይ ይከበራል ብለዋል፡፡

በበዓሉም በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ይቀመጣል፤ መላ ኢትዮጵያዊያንም ከአሁን በፊት እንደሚከበረዉ በአጤ ምኒልክ አደባበይ ተገኝቶ በዓሉን እንዲታደም ነዉ ጥሪያቸዉን ያስተላለፉት፡፡

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በሥራ አፈጻጸማቸው ብልጫ ላሳዩ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ማልበስ መርኃ ግብር አካሄደ።
Next article“ከታሪክ ሽሚያ ወጥቶ አድዋን አድዋ ያደረጉ ጀግኖችን ለማስታወስ የተሠሩ እና የተቀመጡ ማስታዎሻዎችን ክብር ሰጥተን መጠበቅ ይገባናል”