የብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በሥራ አፈጻጸማቸው ብልጫ ላሳዩ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ማልበስ መርኃ ግብር አካሄደ።

121

የካቲት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በሥራ አፈጻጸማቸው ብልጫ ላሳዩ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ማልበስ መርኃ ግብር አካሂዷል።

የማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቦጃ አጋ የዕለቱ ተሿሚዎች የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን አከርካሪ መስበር የሚችሉ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል አመራሮችና አባላት በማሰልጠንና ድጋፍ በመስጠት የተሰጣችሁን አደራና ኃላፊነት በአግባቡ እና በጀግንነት ተወጥታችኋል ብለዋል፡፡ የሠራዊት አባላቱ ለማዕረግ እድገት በመብቃታቸውም እንኳን ደስ አላችሁ ነው ያሉት።

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ልማት ሻለቃ አቡ ኃይሉ በበኩላቸው ፣ አንድ ወታደር የማዕረግ ተሿሚዎች የተሰጣቸው ማዕረግ ለተሻለ የግዳጅ አፈጻጸምና ኃላፊነት መኾኑን በመገንዘብ ለቀጣይ ግዳጅ የበለጠ ጠንክሮ መዘጋጀት እንደሚገባ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“እኛስ አባት አለን ምኒልክ የሚባል እንኳን ተቆጥቶ ዝም ሲል ያባባል”
Next article“የዓድዋ ድል በዓል ምኒልክ አደባባይ ይከበራል” የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር