
ባሕር ዳር: የካቲት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረም ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለሚቀጥሉት 2 ዓመታት የሚኒስትሮች ፎረምን የመምራት ኀላፊነትን ከኬንያ መረከቧ ተገለጸ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል ከኬንያ የሠራተኛና ማኅበራዊ ዋስትና ሚኒስትር ከሲሞን ቼሉጉዊ ጋር ገንቢ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ሚኒስትሯ የሠራተኞች ፍልሰት አስተዳደርን በማሻሻል ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር ገንቢ ውይይት ማካሄዳቸው ገልጸዋል፡፡
ላለፉት ሁለት ዓመታት በኬንያ የተመራ የ11 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት ቀጣናዊ የሠራተኞች ፍልሰት መማክርት የሚኒስትሮች ፎረም በርካታ ተግባራትን ሲያካሄድ መቆየቱም ጠቅሰዋል፡፡
ለዚህም የመሪነቱን ሚና ለተጫወተው የኬንያ መንግሥትና ለፎረሙ አባል ሀገራት ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው ብለዋል ወይዘሮ ሙፈርያት፡፡
በሀገራት የሥራ ገበያ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የሰለጠነ የሰው ኀይል ለገበያ ማቅረብ የሀገራቱን ኢኮኖሚ ከመደገፉም ባሻገር ዜጎች የሚገባቸውን ክብርና ጥቅም እንዲያገኙ እንደሚያስችልም ጠቁመዋል፡፡
በቀጣናዊ የሚኒስቴሮች ፎረም ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የሚኒስትሮች ፎረሙን የመምራት ኀላፊነት ኢትዮጵያ መቀበልዋ ገልጸው የአመራር ሽግግሩ በቅርቡ ይካሄዳል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እንደሌሎች ጉዳዮች ሁሉ በዚህ ዘርፍም የተሰጣትን የመሪነት ሚና ቀጣናዊ ትስስሩን ይበልጥ ለማጠናከርና ፈጣን ለውጥ ለማምጣት ትሰራለች ነው ያሉት፡፡ ኢዜአ እንደዘገበው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/