
የካቲት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪና ሴሬኒ የተመራ የልዑካን ቡድንን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጣሊያን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ያልተቋረጠ የልማት ትብብር ምሥጋና አቅርበዋል። በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የሚያስደንቅ ሥራ እያከናወነ ላለው የጣሊያኑ “ዊ ቢውልድ” (የቀድሞ ሳሊኒ ኢምፕሪጅሎ ኩባንያም) ያላቸውን አድናቆትም ገልፀውላቸዋል።
ወቅታዊውን የሀገሪቱን ሁኔታ በሚመለከትም መንግሥት በሰሜኑ የኢትዮጵያ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ሰላማዊ በኾነ መንገድ ለመቋጨት እየወሰደ ያለውን ዋና ዋና እርምጃዎች በሚመለከትም በዝርዝር አስረድተዋል።
አሸባሪው ሕወሓት በአማራና አፋር ክልሎች ያደረሰውን ጥፋት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ ሰብዓዊ መብት መሥሪያ ቤት የጋራ ምርመራ እንዲያደርጉ
የኢትዮጵያ መንግሥት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
አሸባሪው ቡድን በአጥፊነቱ እንደቀጠለ የገለጹት አቶ ደመቀ በአፋር ክልል እያደረሰ ያለውን ጥፋት በመጥቀስ ለልዑካን ቡድኑ አስገንዝበዋቸዋል።
አሸባሪው ሕወሓት አሁንም ጦር ለመስበቅ በርካታ ወታደሮችን መልሶ በመመልመልና በማሰልጠን ሥራ ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝም አቶ ደመቀ ገልጸዋል፡፡
ጣሊያንን ጨምሮ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት ፀረ-ሰላማዊ አመሉን ለመሸፋፈን የሚያቀርበውን ሐሰተኛ ትርክት መቀበልን እንዲያቆም ጠይቀዋል።
የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪና ሴሬኒ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላም መስፈን እያከናወነ ያለውን ተግባር ሀገራቸው እንደምታደንቅ ተናግረዋል።
ጣሊያን የቀጣናው መሪ ሀገር ከኾነችው ኢትዮጵያ ጋር በልማትና ዲፕሎማሲያዊ ዘርፍ ያላትን ግንኙነት አጠናክራ ማስቀጠል እንደምትፈልግም ገልጸዋል።
ኹለቱ አካላት በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/