
የካቲት 21/2014 ዓ.ም(አሚኮ)የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ጌታቸው አሊ፥ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በሥራ አፈፃፀማቸው ብልጫ በማምጣት ሹመትና ሽልማት ላገኙ የሠራዊት አባላትና አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በማሰልጠኛ ተቋም ሌትና ቀን በመሥራት የሰው ኃይልን ለመገንባት መትጋትን ይጠይቃል ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ ይህንን ኹሉ በማለፍ የሠራዊት አባላቱ ለማዕረግ ሹመትና ሽልማት መብቃታቸውን ገልጸዋል።
ከተሿሚዎች መካከል ሻለቃ እሸቱ ሁሴን እና ሻለቃ መጋቢ ባሻ ጋሪ ገመቹ ባገኙት ሹመት መደሰታቸውን ገልጸዋል። ያገኙት ሹመት ትምህርት ቤቱ በሚያከናውናቸው የስልጠና ሥራዎች በላቀ ተነሳሽነት ለመሥራት መነሳሳት የሚፈጥላቸው መኾኑን ተናግረዋል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አባላት፣ የምዕራብ ጎጃም ዞንና አጎራባች ወረዳዎች የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የፈጸመውን ወረራ ለመቀልበስ በተደረገው የኅልውና ዘመቻ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሠራዊቱን የተቀላቀሉ ወጣቶችን በማሰልጠንና በማብቃት ላሳየው የላቀ ሥራ የእውቅናና የምሥጋና ሰርተፍኬት ከምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ የተበረከተለት መኾኑን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/