
አዲስ አበባ፡ የካቲት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ብናልፍ አንዱዓለም “ብልጽግና ትግል እና ለውጥ የወለደው ፓርቲ ነው” ብለዋል፡፡ ይህ የትግል ለውጥ በአግባቡ እንዲመራና የታለመለትን ስኬት ማምጣት እንዲችል በሪፎርም እንዲመራ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
ውስብስብ የፖለቲካ አካሄድ የነበረበ በመኾኑ ለውጡ በጥናት እንዲመራ ተደርጎ እንደነበር አንስተዋል። ኾኖም ይህ ጥናትና የተግባር ሂደቱ ጥሩ ውጤት ያመጣ ባለመኾኑ ገለልተኛ አካላት እንዲያጠኑት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱንም አቶ ብናልፍ ተናግረዋል።
በጥናትና ግምገማ የኢህአዴግ ግምገማዎች የአራት ድርጅቶች መኾኑና አግላይነቱ ትልቅ ችግር እንደነበር ጠቅሰዋል። በዚህም ሕብረ ብሔራዊ ውህድ ፓርቲ እንዲመሰረት ተደርጓል ነው ያሉት። ሌላው ትልቁ የኢህአዴግ ችግር ዜጎችን በፓርቲ በኩል እንጂ በዜግነታቸው ማሳተፍ አይችልም ነበር፤አሁን ያንን ቀርፈናል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ-ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/