
አዲስ አበባ: የካቲት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ከዓድዋ ድል ምን እንማራለን በሚል መሪ ሃሳብ የፓናል ውይይት በሀገር ፍቅር ቴያትር እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ ምሁራን ተሳትፈዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት ዓድዋ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በልዩ ትኩረት እንድትታይ ከማድረጉ ባለፈ ዲፕሎማሲያዊ ትርፍ ያስገኘ ነው።
የአድዋ ድል ነፃነትን፣ እኩልነትን እና ፍትሕን ለሰው ልጆች ያጎናፀፈ እንደሆነ ነው በመድረኩ የተገለጸው።

ዓድዋ የማይቻሉ የሚመስሉ ችግሮችን መፍታት እንደሚቻል ያሳየ፤ የአይቻልም እና የዝቅተኝነት ስሜትን የሠበረ እንደነበርም ተመላክቷል።
በመሆኑም አሁን እየገጠሙ ላሉ ችግሮችም የዓድዋን ድል የመፍትሔ ቁልፍ ወስዶ መፍታት ላይ ትኩረት እንዲደረግ የመድረኩ ተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡
መድረኩ ላይ የተለያዩ ማኅበራት እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳታፊዎች ኾነዋል፡፡
ዘጋቢ፡-በለጠ ታረቀኝ-ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
