
ባሕር ዳር: የካቲት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገርን እንደ ሀገር ነፃነቷን እና ሉዓላዊነቷን አፅንቶ ለማኖር እና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ተግዳሮቶችን ማለፍ ግድ ይላል፡፡ ኢትዮጵያም በዘመናት ያጋጠሟትን ችግሮች ለመፍታት ውድ ልጆቿ እጅ እና ጓንት በመሆን አስከብረዋት አሁን ላለችበት ደረጃ እንድትደርስ አድርገዋል፡፡ በጀግንነት፣ የሀገርን ክብር ባለማስደፈር እና ቅኝ ገዢዎችን አሳፍሮ በመመለስ በነፃነቷ የፀናች ኢትዮጵያን ለትውልድ አስረክበዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለጥቁር ሕዝቦች ተምሳሌት የሆነች እና ለቅኝ ገዢዎች ያልተንበረከከች የጀግኖች ሀገር ናት ስንል የዓድዋ ድል ዐቢይ ማሳያ ነው፡፡ ታላቁን የዓድዋን ድል ለመቀዳጀት ታላቅ ጀግንነት ተፈጽሟል፤ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነት በር ከፋች በመሆን በታሪክ ይዘከራል፡፡
ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ሁሉን አንድ አድርጎ፣ ለአንድ ዓላማ በማነሳሳት ኢትዮጵያን በጽኑ ዓለት ላይ ፀንታ እንድትቆም አድርጓል፤ ይህም የብዙኃኑን ተሳትፎ እና የጀግንነት ተጋድሎ ገቢራዊ እንዲሆን በማድረጉ ነው፡፡
በዚህ ድል ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጎን ተሰላፊ በመሆን ጉልህ ሚናውን በመወጣት ረገድ የአማራ ሕዝብ በታሪክ ተጠቃሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ ታሪክ ሠሪ ብሎም በተጋድሎው የነፃነት ታሪኩን ጠብቆ እና አስከብሮ የሚኖር ሕዝብ ነው፡፡
በየዘመናቱ የጀግንነት ክብሩን አስጠብቆ በአልደፈር ባይነት የታገለ፣ በሀገሩ እና በማንነቱ የማይደራደር እና ጠላቶቹን ድል መንሳት መገለጫው ያደረገ ኢትዮጵያን ያጸና ሕዝብ ነው፡፡
የአማራ ወጣቶችም ጀግንነትን ከአባቶቻቸው መውረሳቸው ለአንባገነናዊ አገዛዝም ሆነ ሀገር ለመውረር ለሚመጣ ጠላት እንዳይመቹ አድርጓቸዋል፡፡ ለዚህ ማሳያው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሥልጣን ዘመኑ የግፍ በትሩን ለማሳረፍ የዘረጋውን ሴራ በመበጣጠስ እና መቀመቅ እንዲገባ በማድረግ ረገድ አማራ በጽናት ተፋልሟል፡፡
ለአብነት ጥንትም በማንነቱ የማይደራደረው የወልቃይት ጠገዴ አማራ በዚህ ግፍና መከራ ውስጥ ብዙ ተጋድሎችን ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል፡፡
አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ጨቋኝና ጨካኝ አገዛዝ አሽቀንጥሮ ለመጣል ከራሱ አልፎ ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት የወልቃይት ሕዝብ ደማቅ ታሪክ ጽፏል፡፡
ለሽብር ቡድኑ የእግር እሳት በመሆን ከሚቀናጣበት የሥልጣን ወንበሩ ደደቢት ዋሻ ከቶታል፡፡
መላው ኢትዮጵያውያንን ከጎኑ በማድረግ የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን አንባገነናዊ አገዛዝ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ታሪኩ ከኢትዮጵያ ምድር እንዲፋቅ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች አሁንም ተጋድሏቸውን እየፈጸሙ ነው፡፡
የወልቃይት ወጣቶች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጠንካራ የማይበጠስ ገመድ በማሰር አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመደምሰስ እየፈጸሙት ያለው ጀብድ ዘመን አይሽሬ ነው፡፡
የተረጋጋች እና ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር እንዲያስችል ጀግናው የአማራ ሕዝብ አሁንም ጀብድ እየፈጸመ ነው፡፡ የወልቃይት አማራ ወጣቶች በዛ በመከራ ወቅት “ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” ብሎ ከጎናቸው የነበረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በአካል በመገኘት ጭምር እያመሰገኑ ነው፡፡
ኢትዮጵያን ልክ እንደ ጥንቱ ጠላት የማይፈነጭባት፣ ሉዓላዊነቷ የተከበረ፣ እድገቷ ያለምንም ሰላም እጦት እንዲቀጥል ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቆሙ እያስተባበሩ ነው፡፡
አሁንም አማራ ማንነቱ ኢትዮጵያ ሀገሩ የሆነው የወልቃይት ወጣት ውለታን ሳይረሳ በእያንዳንዱ ደጅ እየሄደ ምስጋናውን እየገለጸ ነው።
ለቀጣይ የታሪክ ምዕራፍ የአንድነት ውሉን እያጠበቀ ነው፤ ተቀባዮቹም አቀባበሉን አድምቀውታል፤ እናም የማይናወጥ ቃል ኪዳን እያሠሩ ነው፤ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡
በሄለን ሰፊሁን
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/