
የካቲት 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአየር ኀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ የአየር ኀይሉ አባላት እና አመራሮች አየር ኃይልን ሀገሪቱን በሚመጥን መልኩ ለማደራጀት እየታተሩ ይገኛሉ ብለዋል። አሽባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በመደምሰስ አየር ኀይሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ነው ያሉት።
አየር ኀይሉን በቴክኖሎጅ፣ በሰው ኀይልና በብቃት ከማጎልበት ባሻገር ተቋሙን ለማሳደግ እና ለመጠበቅ የአየር ኀይል ዙሪያ ጥበቃን አስመርቀናል ነው ያሉት።
ዛሬ አሸባሪው ቡድን በከፈተው ጦርነት በጀግንነት ተጋድሎ ለፈጸሙ የሜዳይና የእውቅና ሽልማት ይሰጣቸዋል፤ ይህም ወደፊት አቅምን በማሳደግ የአየር ኀይሉን አገልግሎት ለማጉላት ይረዳል ነው ያሉት ሌተናል ጀነራሉ።
የአየር በረራ እና ተቆጣጣሪ ቴክኒሻኖችን በማሰልጠን ለዚህ ላበቁ የአየር ኀይል አካዳሚ ባለሙያዎችም ምሥጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/