
ከሚሴ: የካቲት 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና በተላላኪው ሸኔ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም በክልልና በፌዴራል ደረጃ የእህትማማች ከተሞች ትስስር ተፈጥሯል።
በተፈጠረው የእህትማማች ከተሞች ትስስር የከሚሴ ከተማ በክልል ደረጃ ከደብረ ማርቆስ በፌዴራል ደረጃ ደግሞ ከሀዋሳ ከተማ ጋር እንዲተሳሰሩ ተደርጓል።
የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድጃ አሊ የተፈጠረው የከተሞች ትስስር የተጎዱ ከተሞችን በፍጥነት ለማቋቋም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የከተሞች ትስስር ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።
ከንቲባዋ በከሚሴ ከተማ በአሸባሪ ቡድኖች የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት፣ የፌዴራል ተቋማትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በርካታ ድጋፍ እያደረጉ መኾኑን ጠቁመዋል፡፡
እህትማማች ከተሞቹም ለመደገፍ እያሳዩት ያለው ፍላጎት የሚደነቅ እንደኾነ ነው የተናገሩት።
ዘጋቢ፡- ሥነጊዮርጊስ ከበደ-ከከሚሴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
