
የካቲት 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ወርኃ ጾሙ ለተፈናቀሉና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የምናደርግበት ሊኾን እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተናገሩ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የዐቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም በግጭቱና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ካለን በማካፈል የችግሮቻቸው ተካፋይ መኾን ይገባል ብለዋል፡፡
ሕዝበ ክርስቲያኑ ወርኃ ጾሙን ከጸብና ከጥላቻ በመራቅ ሊያሳልፈው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የጾሙ ወቅት ምእመኑ ንስሃ የሚገባበት፣ ጥላቻን ከኅሊናው የሚያስወግድበት ፍቅርን በመሻት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበት ሊኾን እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በዚህ ጾም ሕዝበ ክርስቲያኑ ስለሀገር እና ስለቤተክርስቲያን መፀለይ እንደሚገባውም በመልዕክታቸው ማስተላለፋቸውን ፋብኮ ዘግቧል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
