
የካቲት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አምባሳደሮች ተመድበው በሚሄዱባቸው ሀገራት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት በዕውቀትና በሳይንስ የተደገፈ መረጃ መስጠት እንዳለባቸው ተገለፀ።
በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው አምባሳደሮች የኢትዮጵያን ውኃ ፖለቲካና የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
አምባሳደሮቹ በህዳሴ ግድብ ላይ በዳያስፖራዎች መካከል የተፈጠረውን ብሔራዊ ስሜት ለማስጠበቅና የበለጠ ከፍ ለማድረግ በተለየ ትኩረት መሥራት እንዳለባቸውም መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
አምባሳደሮቹ በተሾሙባቸው ሀገራት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ዕውቀት እንዲያጋሩ የማሳተፍ ሥራ እንዲሠሩም እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
