
ደብረ ብርሃን: የካቲት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ወጣቶች አማራን እንወቅ በሚል መርሃግብር በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎችን መጎብኘት ቀጥለዋል።
ወጣቶቹ “በተገኘው ነጻነት ያብራካችን ክፍይ ከሆነው ከአማራ ሕዝብ ጋር በመገናኘታችን ደስታችን ወደር የለውም፤ አሁንም ትግሉ ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም” ነው ያሉት።
“የጉብኝታችንም ዓላማ ኢትዮጵያን ለማጽናት፣ አማራን ለማስቀጠል ዋጋ የከፈለውን እያመሰገንን ለቀጣይ ትግል ወጣቱን ማንቃት ነው” ብለዋል።
ወጣቶቹ ማንነታችንንና ርስታችንን በኀይል በመንጠቅ ግፍ ሲፈጽምብን ከነበረው አሸባሪው ትህነግ መላው የአማራ ሕዝብ ባደረገው ትግል አስመልሰናል፤ የዘመናት ጠላቶቻችን ለመቅበር የምናደርገው ተጋድሎም ከወንድሞቻችን ጋር ይቀጥላል ነው ያሉት
ወጣቶቹ በሰሜን ሸዋ ዞን የነበራቸው ቆይታም የአርበኛ ሞገስ እሸቴና የልጃቸውን ይታገስ እሸቴን ቤተሰቦች በመጠየቅ ተጠናቋል።
ዘጋቢ:–ለአለም ለይኩን
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
