በኢትዮጵያና ሶማሊያ አዋሳኝ ድንበር አካባቢዎች በጸጥታ ጉዳይ አብሮ ለመሥራት ውይይት ተካሄደ።

219

ባሕር ዳር: የካቲት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጁባላንድ ክልል የሰላም ሁኔታ እና በኢትዮጵያና ሶማሊያ አዋሳኝ ድንበር አካባቢዎች በፀጥታ ጉዳይ አብሮ ለመሥራት ውይይት ተካሄደ።

የጁባላንድ ክልል ፕሬዝዳንት፣ የሴክተር 3 አዛዥ፣ የሴክተር 6 አዛዥ፣ የ5ኛ ሞተራይዝድ ዋና አዛዥና የጁባላንድ ክልል ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የመረጃ ኃላፊ በውይይቱ ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል።

ውይይቱን የመሩት የጁባላንድ ክልል ፕሬዝዳንት አህመድ መዶቤ፣ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በታሪክ፣ በባህል፣ በቋንቋ የሚመሳሰሉ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ይህንን አንድነታችንን እና ወንድማማችነታችንን በመሸርሸር ዓላማውን ለማሳካት አልሸባብ ሌት ከቀን እየጣረ ይገኛል ብለዋል።

በመሆኑም እስከ ዶሎ ያሉትን ቦታዎች በመቆጣጠር በጋራ በመሆን መሥራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የሴክተር 3 አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ዘውዱ ሰጥአርጌ፣ በሶማሊያ የጠላት ሽብርተኝነት፣ የጎሳ ግጭት እንዲሁም የፌዴራልና የክልል መንግሥታት አለመግባባት ይስተዋላል ብለዋል።

በተለይ ደግሞ በጌድዮ ዞን በሕዝቡ ዘንድ መረጋጋት እንዳይኖር የሚሰሩትን አካላት በጋራ ሆኖ በመለየት የሀገሪቱን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ ነን ብለዋል።

የአሸባሪ ቡድኑን ሴራ ለማክሸፍ ከሕዝቡ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መስራት እንደሚገባ፤ የአልሸባብን ተንኮልና ሴራ ቀድሞ በመረዳት አከርካሪውን መስበር እንደሚያስፈልግ የሴክተር 6 አዛዥ ብ/ጄ አበባው ሰይድ እና የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮነን መናገራቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተደቀነውን አደጋ በመቀልበሱ ሂደት ምስራቅ ዕዝ አኩሪ የጀግንነት ታሪክ ፈጽሟል” ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Next article“ትግላችን ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ወጣቶች