
ባሕር ዳር: የካቲት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተደቀነውን አደጋ በመቀልበሱ ሂደት ምሥራቅ ዕዝ አኩሪ የጀግንነት ታሪክ መፈጸሙን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።
ኤታማዦር ሹሙ ይህን ያሉት ለምስራቅ ዕዝ ምርጥ አዋጊዎች፣ ተዋጊዎች እና ድጋፍ ሰጪዎች ሜዳይ ከሸለሙ እና ማዕረግ ካለበሱ በኋላ ባደረጉት ንግግር ነው።
በምሥራቅ ዕዝ እና ሌሎች የሠራዊት ክፍሎች ጀግንነትና መስዋእትነት ሀገራችንን ከመፍረስ ማዳንና ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ አንድ አካባቢ እንዲሰባሰብ ማድረግ ተችሏል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ከዕለቱ ተሸላሚዎችም ሆነ እነሱን ካፈራው ምስራቅ ዕዝ ለቀጣይ ተልዕኮ የበለጠ ኃይል ማደራጀት፣ መሠልጠን እና መዘጋጀት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
በሀገር ፍቅሩ የሚታወቀው እና ኢትዮጵያን በመጠበቅ አኩሪ ታሪክ ያለው የአፋር ሕዝብ እንዲሁም ከአብራኩ የወጡ ልዩ ኃይሎችና የሚሊሻ አባላት ከምሥራቅ ዕዝ ጋር በአጋርነት ለፈፀሙት ጀግንነት ኤታማዦር ሹሙ ምስጋና አቅርበዋል።
የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተና ጄነራል መሐመድ ተሰማ በበኩላቸው፣ ዕዛቸው በተሰለፈባቸው በራያ ተራሮች፣ በአማራና በአፋር ክልል ጠላት ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች፣ በጭፍራ፣ በአሳጊታ፣ በቡርቃ እና በዞብል ተራሮች በተደረጉ ውጊያዎች አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡን ተናግረዋል።
ዕዙ የጁንታውን ከንቱ ምኞት በማምከን ሀገሩንና ሕዝቡን በማኩራት በእሳት የተፈተኑ ጀግና አመራርና አባላት ማፍራቱንም አመልክተዋል።
ምስራቅ ዕዝ ለድል መገኘት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግና አዋጊዎች፣ ተዋጊዎች፣ የመስተዳድር አካላት፣ አጋር ክፍሎች እና ግለሰቦችም የእውቅና ሸልማት መስጠቱን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
