
ጎንደር: የካቲት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች በቅኝ ግዛት ለባርነት ሊዳርግ አስቦ የመጣውን የኢጣሊያ ጦርን የካቲት 23/1888 ዓ.ም በሰዓታት ልዩነት ድል ያደረጉበት 126ኛው ዝክረ ዓድዋ በጎንደር እየተከበረ ነው።
ለመላ ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለኾነው ለድል በዓሉ መገኘት በወቅቱ የነበሩ ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
ኢትዮጵያውያን አባቶች ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ክብር ሲሉ በዓድዋ ተራሮች ስር ከጠላት ጋር ተናንቀዋል፤ ድልም አድርገዋል።
በጎንደር ከተማ የፊታችን ረቡዕ የሚከበረውን የዓድዋ የድል በዓል ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሲቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ የማኅበረ- ቅዱሳን ጎንደር ማዕከል የተዘጋጀ ነው። በዋናነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዓድዋ ጦርነትን የነበራት ሚና ላይ ያተኮረ ነው። እንደ ሀገር ኢትዮጵያ የግዛት ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ እንድትቆይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ድርሻ ላቅ ያለ እንደኾነ ታሪክ ያስረዳል።
በውይይቱ እንደተነሳው የዓድዋ ድል፥ የራሳችን ቋንቋ፣ ባሕልና ሰንደቅ ዓላማ ሳይበረዝ እንዲኖረን ጀግኖች አባቶቻችና እናቶች የከፈሉት ዋጋ ነው።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅድመ ዓድዋና በድህረ ዓድዋ ወቅት የነበራት ሚና ከፍተኛ እንደነበርም ተጠቁሟል።
ፊደል ቀርፃ፣ ቀለም በጥብጣና ታሪክን ሰንዳ ለትውልድ በማስተላለፍ፣ ስለ ሀገር ክብርና አንድነት የምታስተምርበት ክብረ ነገሥታዊ በሕግና ሥርዓት ዘርግታ መቆየቷም ተነስቷል።
በቤተክርስቲያኗ መዋቅሮች ኹሉም ሰው ጦርነቱ አይቀሬ መኾኑን እንዲረዳና እንዲዘጋጅ በማንቃት በኩልም ክርስቲያንን ያበረከተችው ሚና ላቅ ያለ ነበር።
በግዛት ይገባኛል ምክንያት ተኳርፈው የነበሩ መሳፍንት በማስታረቅ፣ ወደ አንድነት በማምጣት ስለ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ተባብረው ጠላትን እንዲያንበረክኩ በማድረግ በኩልም አይተኬ ሚና እንደነበራት ተጠቁሟል።
ቤተክርስቲያኗ በጦርነቱ ወቅት የጦር ሰፈሩን በመንደፍ ወራሪውን ኃይል ለመውጋት የሚያስችሉ ወታደራዊ አሰላለፍ እንዲኖር በማድረግ በኩልም በጎ ተጽዕኖ እንደነበራት ተገልጿል ።
የዓድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የተከበረው ድሉ ከተፈጸመ ሰባት ዓመት በኋላ በ1895 ዓ.ም ነው። ሲከበርም ለኹሉም ጀግኖች ሰማእታት ተዝካር በማውጣት ነበር።
ዘጋቢ:- ጳውሎስ አየለ-ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
