የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ወጣቶች አቀባበል አደረገ።

372

የካቲት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ወጣቶች በፍቼ ከተማ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

“የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው” ብሎ ግንባሩን ለጥይት የሰጠው በለውጡም ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር አብሮ ከጎኑ የቆመው የወንድም የአማራ ሕዝብ የወልቃይት ወጣቶች ኦሮሚያ ክልል ሲደርሱ በፍቼ ከተማ አስተዳደር እና አባገዳዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ አቀባበል ተደርጓላቸዋል። የክልሉ መንግሥት የምሳ ግብዣም አድርጎላቸዋል።

ወጣቶቹ በክልላቸው የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ዛሬ ወደ ሰሜን ሸዋ እያቀኑ ሲሆን “የአማራ ወጣቶች አማራን እንወቅ” በሚል መሪ ሐሳብ በዚህ ሳምንት እየተካሄደ በሚገኘው የታሪካዊ እና የቱሪዝም ስፍራዎች ጉብኝት እና የወንድማማችነት መርኃ ግብር ደብረ ብርሃን ከተማ ሲደርሱም ልዩ ልዩ መርኃ ግብሮች እንደሚከናወኑ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየሀገርን ሰላም ለማደፍረስ እረፍት አልባ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በቅንጅት መደምሰስ እንደሚገባ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር አመላከቱ፡፡
Next articleየመከላከያ ሕብረት ሎጂስቲክስ ሜንተናንስ መምሪያ በሕግ ማስከበር እና በኅልውና ዘመቻው የላቀ የሥራ አፈፃፀም ላላቸው ክፍሎች እና ግለሰቦች ዕውቅና እና የማዕረግ ማልበስ መርኃግብር አካሄደ፡፡