የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ እረፍት አልባ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በቅንጅት መደምሰስ እንደሚገባ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር አመላከቱ፡፡

145

ባሕር ዳር: የካቲት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ እረፍት አልባ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በቅንጅት መደምሰስ እንደሚገባ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስ ምሑር አመላክተዋል፡፡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምሕር ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የሚያደርገው ትንኮሳና ወረራ የክልሎች ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መወሰድ እንደማይገባው ተናግረዋል፡፡
የፌዴራሉ መንግሥት ኪሳራ በማያደርስ አግባብ አሸባሪው ቡድን የሚደመሰስበትን መንገድ መከተል ይገባልም ብለዋል፡፡ የክልል መንግሥታት የፀጥታ ኀይሎችም ለዳግም ወረራ የሚንቀሳቀሰውን የሽብር ቡድን ባሉት አማራጮች ሁሉ መደምሰስ እንደሚገባ ምሁሩ ተናግረዋል፡፡ የጠላትን ዝግጅት አስቀድሞ ማክሸፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው እያንዳንዱ የማኅበረሰብ ክፍል የጠላትን እንቅስቃሴ በመከታተል መረጃ ከመስጠት ባለፈ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ኾኖ እርምጃ እስከመውሰድ መድረስ እንደሚገባውም ገልጸዋል፡፡ ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ጠላት ሕዝብን ሰላም ለመንሳት የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች በመከታተል በሥነ ልቦና የተዘጋጀ መሆን መቻል አለበትም ብለዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ የሚያደርሰውን ሰብዓዊ ጉዳት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አጉልቶ ማሳዬት የሚጠበቅ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግብዓት የሚሆኑና በዲፕሎማሲው ረገድ ዋጋ የሚሰጣቸውን ጉዳቶች አጉልቶ ማቅረብ እንደሚገባ ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ጠቁመዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አረመኔያዊ ተግባር ውስጥ እንዳለ ማሳየት አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ የሽብር ቡድኑን በጋራ መፋለምና ማጥፋት እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ እና የተሟላ ጤና ያለው ወጣት ወደ መከላከያ ሠራዊትና ወደ ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች እየተቀላቀለ ብቁ መሆን አለበት ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
የታጠቀ፣ የሰለጠነና በሥነ ልቦናው በአግባቡ የተቃኘ ሕዝብ መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡
ረዳት ፕሮፌሰሩ እንዳሉት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጋር የሚደረገው ውጊያ እንዳለቀ ተደርጎ መነገር የለበትም፤ መነገር ያለባቸው እውነታዎች እየተነገሩ የትግሉ ጉዳይ አጀንዳ እንደሆነ መቀጠል አለበት፡፡ በአማራ ክልል ከጠላት ጋር የሚደረገው ትግል የመጀመሪያ አጀንዳ ቀጥሎም መልሶ መገንባትና ኢኮኖሚውን ማሳደግ መሆን እንዳለበትም ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ገልጸዋል፡፡
የአማራ ሕዝብ ጠላቱን ማጥፋት ግድ እንደሚለው ነው የተናገሩት፡፡ የአማራ ሕዝብ በውስጣዊ አንድነቱ ላይ የሚመጡበትን እኩይ አጀንዳዎች በመፍታት በአንድነት መቆም እንዳለበትም ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው አሳስበዋል፡፡ በውስጡ የሚነሱ ጉዳዮችን በንግግርና በምክክር መፍታት ይገባልም ነው ያሉት፡፡ ትግሉ ውጤታማ የሚሆነው በእዝ ሰንሰለት ሲሆንና ከፖለቲካ መሪዎች ጋር ተግባብቶ መሥራት ሲቻል እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የእንግዳ ማረፊያ ነበረ ቤታቸው፤ ኖሩ በዋሻ ውስጥ ዘመን ቢገፋቸው”
Next articleየኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ወጣቶች አቀባበል አደረገ።