“ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የታችኛው ተፋሰሱ ሀገራት በትብብር ሊሠሩ ይገባል” በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሳማድ አሊ ላኪዛዴህ

113

የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ የቀጠናውም ሀገራት ተጠቃሚ እንዲኾኑ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በትብብር ሊሠሩ እንደሚገባ በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሳማድ አሊ ላኪዛዴህ ገለጹ።

በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሳማድ አሊ ላኪዛዴህ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ልማቷን ለመደገፍ የምትገነባውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ኢራን ትደግፋለች ብለዋል።

ግድቡም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይኾን ለጎረቤት ሀገራትና ለቀጣናውም ጭምር በርካታ ጥቅም እንዳለው ገልጸው ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ መሥራት ይገባል ነው ያሉት።

በተለይም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በዚህ ረገድ በትብብር ሊሠሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

“እኛ ኹሉንም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በጋራ እንዲሠሩና እውነተኛ ውይይት እንዲያደርጉ፣ ሰላማዊ ድርድር እንዲያደርጉና ይሄ ትልቅ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን ለኹሉም የተፋሰሱ ሀገራት ጥቅም እንዲሰጥ እንመክራለን” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለሕዝቧ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ የመገንባት መብት እንዳላት ጠቁመዋል።

“ኢትዮጵያ ሃብቷን ለሕዝቡ ጥቅም ለማዋል የምታደርገውን ጥረት እንደግፋለን፤ ግድቡም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን ለጎረቤትም ሀገራት ጭምር የሚጠቅም ነው” ብለዋል።

በኢትዮጵያ ተደጋጋሚ የመብራት ኃይል መቆራረጥ እንደሚገጥም ገልጸው የግድቡም ኃይል ማመንጨት ይህንን ችግር እንደሚያቃልለው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ እንደሚገኝ አንድ ዲፕሎማትም በከተማዋ ያለውን የኃይል መቆራረጥ ማስተዋላቸውን ገልጸው ግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ትልቅ እምርታ አለው ብለዋል።

የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በውኃው የመጠቀም መብት እንዳላቸው ጠቁመው ኹሉም የተፋሰሱ ሀገራት ውኃውን በትብብር አልምተው መጠቀም እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ብዙ ጊዜ ሱዳን ወይም ደግሞ ግብጽ ከፍተኛ ጎርፍ እያጋጠማቸው እንደሆነ እሰማለሁ፤ ስለዚህም ይህ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረበ ብቻ ሳይሆኾን ጎርፍም በመከላከል ረገድና በተለይም ከወንዙ በሚመጡ ሌሎች አሉታዊ ተጽዕኖዎች በመከላከል ረገድ ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል ብለዋል።

አሁን ላይ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ84 በመቶ የደረሰ ሲኾን ባለፈው ሳምንት የግድቡ አንደኛው ተርባይን 375 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየደቡብ ዕዝ የ21ኛ ክፍለ ጦር ጀብድ ለፈጸሙ የሠራዊት አመራሮችና አባላት የሜዳይ ሽልማት እና ማዕረግ እድገት ሰጠ፡፡
Next article“አምባሳደሮች የተሰጣቸውን ተልዕኮ የሚመጥን ሥራ አሟልተው መሥራት አለባቸው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን