የደቡብ ዕዝ የ21ኛ ክፍለ ጦር ጀብድ ለፈጸሙ የሠራዊት አመራሮችና አባላት የሜዳይ ሽልማት እና ማዕረግ እድገት ሰጠ፡፡

235

የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሀገር የማፍረስ ዕኩይ ዓላማው እንዳይሳካ በተካሄደው የኅልውና ዘመቻ የመከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ ኀይሎች ታሪክ የማይረሳው ጀብድ ፈጽመዋል። ከነዚህ የሀገር ባለውለታዎች መካከልም የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ሠራዊት አመራሮችና አባላት ይገኙበታል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ 21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ጀብድ ለፈጸሙ የሠራዊት አባላትና የክፍለ ጦሩ አመራሮች የሜዳይ ሽልማትና የማዕረግ እድገት ሰጥቷል። የተሰጣቸው የጀግና ሜዳይ ሽልማትና የማዕረግ እድገት እንዳስደሰታቸውና ለቀጣይ ግዳጅ የበለጠ ዝግጁ እንዲኾኑ መነሳሳት እንደሚፈጥር የዕለቱ ሜዳይ ተሸላሚና የማዕረግ ዕድገት የተሰጣቸው የሠራዊት አባላትና የክፍለ ጦሩ አመራሮች ለአሚኮ ተናግረዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተክሉ ሁሪሳ እንዳሉት የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመኾን የትህነግ የሽብር ቡድን እንዲደመሰስ ታላቅ ታጋድሎ አድርገዋል። ለከፈሉት መስዋእትነትም ኢትዮጵያና ሕዝቧ ሲያመሰግኗቸው ይኖራሉ ብለዋል።
የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሰለሞን ኢተፋ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላትና አመራሮች በኅልውና ዘመቻው ወቅት የፈጸሙት ጀብድ የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡ ለተገኘው ድል የሕዝቡ ሚና ትልቅ እንደነበረም ተናግረዋል።
ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የጦርነት ትንኮሳ በመቀጠሉ ከእስካሁኑ የበለጠ ዝግጅት እንደሚያስፈልግና ሠራዊቱም ለዚሁ ግዳጅ ራሱን ብቁ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡-አሊ ይመር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየማዕከላዊ ዕዝ የሠራዊት መሪዎችና አባላት ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር የአፈር እቀባና የእርከን ሥራ አከናወኑ።
Next article“ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የታችኛው ተፋሰሱ ሀገራት በትብብር ሊሠሩ ይገባል” በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሳማድ አሊ ላኪዛዴህ