
የማዕከላዊ ዕዝ የሠራዊት መሪዎችና አባላት ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር የአፈር እቀባና የእርከን ሥራ አከናወኑ።
ሰቆጣ፡ የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ዕዝ የሠራዊት መሪዎችና አባላት ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር የአፈር እቀባና የእርከን ሥራ አከናውነዋል።
የዕዙ ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ኮሎኔል ረሽድ ሐሰን “መከላከያ ኃይላችን በደሙ የሀገሩን ነፃነት እያስከበረ ከተልዕኮው በተጓዳኝ ልማታዊ ሥራዎች ላይ በሚያደርገው ተሳትፎ በላቡ የሕዝብን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል” ብለዋል።
የዕዙ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ተወካይ ኮሎኔል አበበ መንግሥቱ በበኩላቸው የሕዝብና የሠራዊቱን ትብብር የሚያጠናክሩ ልማታዊ ተግባሮችን በጋራ ማከናወናችን የሚያጋጥመንን ማንኛውንም ሀገራዊ ጠላት በተባበረ ክንዳችን ድል ለማድረግ ያስችለናል ነው ያሉት።

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነፃነት ወንድሙ “የተራቆቱ መሬቶችን ለማልማትና በጐርፍ የሚሸረሸረውን ለም አፈር በማቀብ ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን በደለል እንዳይሞላ ለማድረግ እና የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ ሕዝቡና ሠራዊታችን ተቀናጅቶ ሲሠራ የሀገራችን ብልፅግና ይረጋገጣል” ብለዋል።
በልማታዊ ሥራው ላይ ከተሳተፉት መካከል አስር አለቃ ዓለማየሁ እሸቴ እና ወይዘሪት አድና ግርማይ የልማት ሥራዎችን ተቀናጅተን እየፈፀምን ሰላም የሰፈነባትን ሀገር ለመገንባት ሀገር አፍራሽ አሸባሪ ቡድኖችን በትብብር እናጠፋለን ሲሉ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
