
ባሕር ዳር: የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አመልድ ኢትዮጵያ የድርጅቱን ሀብት እና ንብረት በመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የድርጅቱ ሠራተኞች እና ተባባሪ አካላት ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።
የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አለማየሁ ዋሴ (ዶ.ር) አመልድ ኢትዮጵያ የወደመበትን ሀብት እና ንብረት ብቻ ሳይሆን በሚያገለግለው ሕዝብ ላይ የደረሠውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውድመት በልማት ለመተካት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዶክተር አለማየሁ አመልድ ኢትዮጵያ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ከ87 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሐብት እንደወደመበት ተናግረዋል፡፡

በድርጅቱ ሠራተኞች፣ በአካባቢው ማኅበረሰብ እና በሃይማኖት ተቋማት ትብብር ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ከውድመት ማዳን መቻሉን ድርጅቱ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡንም ገልጸዋል፡፡
ሥራ አስኪያጁ ዕውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው ሰዎች ሕይዎታቸውን ቀብድ አስይዘው መስዋእትነትን የከፈሉ ናቸው፤ ለዚኽም ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በሽልማቱ 38 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ሌሎች አካላትም ይህንን በጎ ተግባር ትምሕርት በመውሰድ ሠራተኞቻቸውን ሊያበረታቱ ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
