ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ እና የሚታዩ የአሠራር ክፍተቶችን ለመቅረፍ በጋራ እንደሚሠሩ የአማራ ክልል ገንዘብ እና ገቢዎች ቢሮ አስታወቁ።

173

ደሴ: የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ውድመት የደረሰበትን የሕዝብ ሀብት እንዳይባክን ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ እና የሚታዩ የአሠራር ክፍተቶችን ለመቅረፍ በጋራ እንደሚሠሩ የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ እና ገቢዎች ቢሮ አስታውቀዋል። ተቋማቱ ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ ምክክር አካሂደዋል፡፡
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ጥላሁን መሃሪ ተቋማቱ ቅንጅታዊ አሠራራቸውን በማጠናከር ለክልሉ ልማት በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ከወጪ እና ገቢ ጋር ተያይዞ በተቋማቱ ይሰተዋሉ የነበሩ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት የጋራ አሠራርን በመዘርጋት እንደሚሠሩም የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ፀጋ ጥበቡ ገልጸዋል።
የክልሉ ገንዘብ ቢሮ እና ገቢዎች ቢሮ ያሉባቸውን ችግሮች በጋራ በመፍታት የክልሉን ገቢ ማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድም ይፈራረማሉ ተብሏል። በኮምቦልቻ ከተማ በተካሄደው የምክክር መድረክ የዞን፣ የከተማ አስተዳደር እና የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቤተልሔም ሰለሞን- ከኮምቦልቻ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች አንድ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
Next article“የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ ባለፉት 15 ወራት በደም የተገኘ ነጻነቱን መብራት፤ የናፈቀውን እውነተኛ ማንነቱን እራት አድርጎ በጽናት ይጠብቃል” ዋና አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው