በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች አንድ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

186

ከሚሴ: የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በመገኘት በወራሪው የትግራይ ቡድን ለተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች አንድ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ለአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ድጋፍ አድርጓል።
የአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን አስተዳዳሪ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና ተላላኪው ሸኔ ከደረሰበት ጉዳት ሳያገግም የአፋር ክልል ጉዳት ጉዳቴ ነው በማለት ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
ዋና አስተዳዳሪው የገቢረሱ ዞን ከአማራ ክልል ጋር አዋሳኝ መሆኑን በመጥቀስ አሁን ላይ በአካባቢው ያለው ሰላም አስተማማኝ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ሰላሙን ለማስቀጠል በትብብር ይሠራል ብለዋል።
የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ኀላፊ መሀመድ ሁሴን በክልሉ አሁን ላይ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ወገኖች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያዎች እንደሚገኙ ተናግረዋል። ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ መላው ኢትዮጵያዊያን ደጀንነታቸውን እያሳዩ ነው ብለዋል።
የቢሮ ኀላፊው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአፋር ክልል አሁንም ከጥፋቱ ሳይማር ወረራ ለመፈፀም ሙከራ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አህመድ አሊ የተደረገው ድጋፍ ከደረሰው ጉዳት አንፃር በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል፤ በቀጣይ ድጋፉ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
ወራሪውን ቡድን ለመደምሰስ የአፋር ክልል የሚያደርገውን ትግል እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
ዋና አስተዳዳሪው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ከአፋር ክልል አጎራባች ወረዳዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥልና የጥፋት ቡድኖችን በትብብር እንደሚያጠፉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:–ይማም ኢብራሄም
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ አሁን ያገኘውን ነጻነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዞናችን ያልተቋረጠ ድጋፍ ያደርጋል” የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ
Next articleኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ እና የሚታዩ የአሠራር ክፍተቶችን ለመቅረፍ በጋራ እንደሚሠሩ የአማራ ክልል ገንዘብ እና ገቢዎች ቢሮ አስታወቁ።