“የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ አሁን ያገኘውን ነጻነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዞናችን ያልተቋረጠ ድጋፍ ያደርጋል” የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ

159

የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ወጣቶች በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ ሲደርሱ በዞን አሥተዳደር የአመራር አካላትና በማኅበረሰቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የተውጣጡ ወጣቶች አሁን ለተገኘው የማንነት ነጻነት በተግባር በመታገል አጋርነቱን ላሳየው የምዕራብ ጎጃም ዞን ሕዝብ ምስጋና ለማቅረብና የባህልና ኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ጉበኝት ነው ያደረጉት።
አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ላለፉት በርካታ ዓመታት የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ አማራዊ ማንነትን በኀይል ለመንጠቅ ግፎችን መፈጸሙን ወጣቶቹ ከዞኑ የአመራር አካላትና ከቡሬ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ወቅት ገልጸዋል። ወጣቶቹ አሁን ለተገኘው የነጻነት ቱርፋት ከእኛ ባሻገር የአማራ ወጣቶች “ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” በማለት የህይዎት መስዋእትነት በመክፈላቸው ያላቸውን ክብርና ምስጋና አቅርበዋል።
በውይይት መድረኩ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ አቶ አለባቸው ገነቱ አሸባሪው ቡድን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ ላለፉት ዓመታት በኀይል ማንነቱ ተረግጦ ቆይቷል ብለዋል። አሁን ለመጣው ነጻነትም የአማራ ሕዝብ እስከ ህይዎት መስዋእትነት በመክፈል ታግሏል ነው ያሉት።

አማራዊ አንድነትን በማጠናከር የመጣውን ለውጥና ነጻነት በማጽናት አሸባሪውን የትህነግ ቡድንን ማጥፋት እንደሚገባ የተናገረው ደግሞ የአማራ ክልል ብልጽግና ወጣቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጋሻው ተቀባ ነው።
በቀጣይም ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶችን ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞንን እንዲጎበኙ በማድረግ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ትስስር ለማጠናከር ይሠራል ብሏል።
“የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ አሁን ያገኘውን ነጻነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዞናችን ያልተቋረጠ ድጋፍ ያደርጋል” ያሉት ደግሞ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ ናቸው።
ወጣቶቹ በቆይታቸው ከእርስ በርስ የውይይት መርሃግብሩ ባሻገር የባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ንብረት የሆነውን የፊቤላ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ዘመኑ ይርጋ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
Amhara Media Corporation – YouTube
youtube.com

Previous articleሰሞኑን በብራሰልስ እና ሙኒክ የተካሄዱት ጉባኤዎች የኢትዮጵያን ጥቅሞች ማስከበር በሚያስችል መልኩ መጠቀም እንደተቻለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
Next articleበአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች አንድ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።