ሰሞኑን በብራሰልስ እና ሙኒክ የተካሄዱት ጉባኤዎች የኢትዮጵያን ጥቅሞች ማስከበር በሚያስችል መልኩ መጠቀም እንደተቻለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

93

አዲስ አበባ: የካቲት 17/2014 ዓ.ም(አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው አንዳሉት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ የአውሮፓ አፍሪካ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን ፍላጎት እና የወቅቱን ሁኔታ አስረድቷል ብለዋል። አውሮፓ እና አፍሪካ ሊተባበሩባቸው የሚችሉ ጉዳዮች በመድረኩ ተነስቷል ነው ያሉት አምባሳደር ዲና።
ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከጀርመን፣ ከፈረንሳይ፣ ከስሎቫኒያ፣ ከስፔን እና ከፓርቹጋል ሀገራት መሪዎች ጋር የኹለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል ነው ያሉት፡፡
አፍሪካን ለሽብርተኝነት፣ ለፅንፈኝነት እና ለግጭት የሚያጋልጧትን ጉዳዮች እንደገና ታጢን በሚል መሪ ሐሳብ በጀርመን ሙኒክ በተካሄደው የጣና ፎረም ላይ ኢትዮጵያ መሳተፏን አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የዘር ግጭቶች፣ ምርጫ እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነት የአፍሪካን ቀንድ ሰላም እንደሚያውክ ለጉባኤው ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ደመቀ በጉባኤው የቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ግንኙነት ማሳደግ እና ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ ገልጸው ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ፎረም መገለሏ ስሕተት አንደነበር ገልጸዋል።
ከዋናው ውይይት በተጓዳኝ ከስዊዲን፣ ከአይርላንድ እና ከጀርመን መሪዎች ጋር በኹለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይት ማድረጋቸውንም አምባሳደሩ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን – ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአማራ ክልል መንግሥት በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ተቋማትን ለሚመሩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመቶችን ሰጠ፡፡
Next article“የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ አሁን ያገኘውን ነጻነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዞናችን ያልተቋረጠ ድጋፍ ያደርጋል” የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ