ኢትዮጵያ እና ሩስያ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የነበሯቸውን ትብብሮች እና ውሎች በአዲስ የትግበራ ምዕራፍ ለማስቀጠል ተስማሙ።

249

የካቲት 17/2014 ዓ.ም(አሚኮ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ የሩስያ ፌደሬሽን ፓርላማ ሴናተር ኢጎር መሮዞቭ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
ከአንድ ምዕተ ዓመት ተኩል በላይ የዘለቀውን የሀገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት በቴክኖሎጂው ዘርፍ የኹለትዮሽ ተጠቃሚነትን በሚረጋግጥ መልኩ ማስቀጠል እንደሚገባ ዶክተር በለጠ ገልጸዋል።
የሩስያ ፌደሬሽን ሴናተር ኢጎር መሮዞቭ ሩስያ በስፔስ ቴክኖሎጂ፣ በስማርት ከተማ ፕሮጀክት ግንባታ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ኒውክለርን ለሰላም በመጠቀም ረገድ፣ በፋርማሲ ቴክኖሎጂ፣ በንግድ በኢንቨስትመንትና በሌሎች የኹለትዮሽ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ያላትን አቅም ለማካፈልና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመሥራት መንግሥታቸው ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አብራርተዋል።
በተለይም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎትን በሩስያ ከተሞች ኹሉ ለማዳረስ የግሎናስ ዓለምአቀፍ ጂፒኤስ ያስገኘውን ፋይዳ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የሩስያ ፌደሬሽን አምባሳደር ኢቭኒ ተርኪሂን በበኩላቸው ኢትዮጵያና ሩስያ በስማርት ሲቲ ፕሮጀክት፣ በጸጥታና ደኅንነት እንዲሁም በትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችሉ ተግባራትን በአጭር ጊዜ ወደ ሥራ እናስገባለን ብለዋል፡፡
የኢትዮ ሩስያ የኹለትዮሽ የመንግሥታት ፎረምን (Ethio-Russia Intergovernmental Forum) ከኢትዮጵያ በኩል በሊቀመንበርነት እንዲመሩ ዶክተር በለጠ ሞላ በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል መወከላቸው እንዳስደሰታቸው አምባሳደሩ አውስተው በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ይሄው የበይነ መንግሥታቱ የኹለትዮሽ የጋራ መድረክ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የሩስያ ፌደሬሽን ኢትዮጵያ በገጠማት ችግር ኹሉ በወሳኝ ግዜያት ከጎኗ መቆሟን ያመሰገኑት ዶክተር በለጠ፥ የሩስያ ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋዕለንዋያቸውን እንዲያፈሱና ያልተነካውን እምቅ አቅም በማውጣት የኹለቱን ሀገራት ሕዝቦች ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በውይይታቸውም ካሁን ቀደም ያሉ ስምምነቶችን በማጠናከር ቀጣይ ግንኙነቶችን እና የትብብር ማዕቀፍን ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን በመለየት ወደ ተጨባጭ እንቅስቃሴ ለመግባት ስምምነት ላይ
መደረሱን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአፍሪካና ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ።
Next articleየአማራ ክልል መንግሥት በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ተቋማትን ለሚመሩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመቶችን ሰጠ፡፡