
የካቲት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የኢንቨስትመንት ቦርድ፣ ከኢስላማባድ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት፣ ስትራቴጂክ ጥናት ተቋም ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በወይይታቸውም የኢስላማባድ ንግድና ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የንግዱ ማኅበረሰብ ጋር የተለያዩ ምርቶች በመሸጥና በሽርክና ለመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቻው ገልጸዋል፡፡ ይህንኑ ግንኙነት የተሳካ ለማድረግ ለንግዱ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል፡፡
አምባሳደር ሬድዋን በበኩላቸው የመዳረሻ ቪዛ የማመቻቸት ሥራ ታሳቢ በማድረግ እንደሚሠራ ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካራቺ የሚያደርገውን ቀጥታ በረራ በሂደት ላይ መኾኑንም አውስተዋል፡፡ የፓኪስታን ባላሃብቶች በግብርና፣ በፋርማሲዩቲካል፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በምርት ማቀነባበርና ጨርቃጨርቅ ዘርፍ ላይ በኢትዮጵያ መዋዕለንዋያቸውን እንዲያውሉ አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የኢንቨስትመንት ሊቀመንበር መሐመድ አዝፋር ጋር በተደረገ ውይይት ፓኪስታን በአፍሪካ ለምታደርገው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያንዋና አጋር የማድረግ ፍላጎት እንዳለቸው ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ሬድዋን ኢትዮጵያ በፓኪስታን ኤምባሲዋን ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኗን ገልጸዋል፡፡
የኹለቱ ሀገራት የንግድ ማኅበራት መደበኛ ትስስርና ግንኙነት የሚፈጥሩበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል፡፡
የኢንቨስትመንት ቦርድ ሊቀመንበሩ እ.ኤ.አ ከመጋቢት 30-31/ 2022 በፓኪስታን በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ጉባኤ የኢትዮጵያ ባለሃብቶች እንዲሳተፉ ግብዣ አስተላልፈዋል፡፡
በአምባሳደር ሬድዋን የሚመራው ልዑክ ከኢስላማባድ ስትራቴጂክ ጥናት ተቋም ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ኹለቱ ሀገራት ያሉ እምቅ የኢኮኖሚ አቅም የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ በሰፊው መሥራት እንደሚያስፈልግ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
በትምህርትና ተቋማዊ ትስስር ላይ በትብብር መሥራት እንደሚያሰፍልግም መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
